ዛሬ ዉጊያዉን ማሸነፍ ትችላለህ

ዛሬ ዉጊያዉን ማሸነፍ ትችላለህ

ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። – ሮሜ 8:6

አሁን በዚህ ሰዓት እኔና እናንተ በዉጊያ መኃል ነን፡፡ ዉጊያዉ መንፈሳዊ ዉጊያ ነዉ እኛም የምንፋለመዉ ከጨለማዉ ዓለም ገዢዎች ከመንፈሳዊያን ሰራዊቶች ጋር ነዉ (ኤፌ 6፡12)፡፡ ጦርነቱን ለማሸነፍ የመንፈስ ቅዱስ ልብ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡

የሚያሳዝነው ነገር በሥጋቸዉ እያሰቡ የሚኖሩ ብዙ አማኞች መኖራቸዉ ነዉ፡፡ ዓለማችንን በሚለዉጥ መንገድ መኖር ከፈለግን በስጋ መኖርን አቁመን በመንፈስ እየተመራን መኖር መጀመር አለብን፡፡

ሁላችንም የስጋ ፍላጎቶቻችንን ስሜታችንና አእምሮአችን እንዲመራን በመስፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ማዋል ይጠበቅብናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለን ስጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በስጋ ላይ ጦርነተ እንደሚያዉጁ ነዉ፡፡ ስለዚህ መንፈስና ስጋ በዘላቂነት እርስ በእርስ ይቀራናሉ ማለት ነዉ፡፡

ጦርነት ነዉ! ዲያብሎስ ይጠላናል ለስጋ እጃችንን እንድንሰጥ ያለማቋረጥ ይሰራል፡፡

በመጨረሻም ማን በህይወትህ ውስጥ እንደሚያሸንፍ የምትወስነዉ አንተ ነህ፡፡ መልካሙ ዜና ለሥጋህ መገዛት የለብህም፡፡ የስጋን ፈቃድ በቁጥጥሩ ስር በማድረግ በመንፈስ መኖር ትችላለህ፡፡ ዉጊያዉን ዛሬ ማሸነፍ ትችላለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ ዉጊያዉን ማሸነፍ እፈልጋለሁ፡፡ መንፈስና ሰላም የሆነዉ የመንፈስ ቅዱስ ልብ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ፡፡ ዛሬ መንፈስህን እመርጣለሁ፡፡ ስጋዬን ወደ ፈቃድህ እንዳመጣ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon