ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? – ማቴ 16፡26
ሰይጣን ዝቅተኛ ኑሮ እንድንኖር እግዚአብሔር ግን ወደ ከፍታ እንድንመጣ ይፈትኑናል፡፡ ልንሰራዉ ከምንችለዉ ከባድ ስህተት አንዱ አሁን በእጃችን ያለዉ ነገር ጥሩ ነዉ ማለት ወይም ማድረግ የምንችለዉ ትልቁ ነገር ይህ ነዉ ብሎ ማሰብ ነዉ፡፡ ዝቅተኛ አስተሳሰብ ወደ ኋላ ይጎትተናል ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚሰራዉ እርሱ እንደሚሰራ በምናምነዉ ልክ ነዉና፡፡
በመንፈሳዊነታችሁ “በቂ ነዉ” በሚባለዉ ቦታ ላለመገኘት ተጠንቀቁ፡፡ መካከለኛ መሆን አልፈልግም ምክንያቱም የማገለግለዉ እግዚአብሔር መካከለኛ አይደለምና፡፡ እግዚአብሔር የልህቀት አምላክ ነዉ ስለዚህ ልከተለዉ እፈልጋለሁ፡፡ ከላይ ያለዉ ቃል እምደሚናገረዉ ዓለም የምታቀርብልንን ሁሉ ልናገኝ እንችላለን ግን እርሱ ለእኛ ያለዉን የበረከት ሕይወት አጥተን እናበቃለን፡፡
ዝቅተኛ ኑሮ ከፍተኛ ዋጋ አለዉ፡፡ በኢየሱስ ያገኘነዉን መልካም ፣ ሰላማዊ ፣ የጽድቅና በደስታ የተሞላ ሕይወት ሊሰጠን የሚችል ነገር በዓለም የለም፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመቃወም እንደልብህ እየኖርክ ከሆነ የምትኖረዉ ኑሮ ዝቅተኛ ነዉ፡፡
እግዚአብሔር እንድትባረክ ይፈልጋል ግን ደግሞ በረከቱን ራስህ ለራስህ እንድታቀርብ አይፈልግም፡፡ እርሱ ነገሮችን ከእርሱ በላይ እንድታስቀምጥ አይፈልግም፡፡ አስተዉል እኛ እርሱንና መንግስቱን አስቀድመን ስንሻ እርሱ ለእኛ በመጋዘን ያስቀመጠዉን በረከት ማምጣት ይጀምራል፡፡ ይህ ነዉ ከፍተኛ ሕይወት መኖር ማለት፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! ለዝቅተኛ ሕይወት መኖር አልፈልግም፡፡ የመንግስትህን ከፍተኛ ኑሮ መኖር እንድችል ትኩረቴን አንተ ላይ እንዳደርግ እርዳኝ፡፡