የሁልጊዜ የአንተ ወዳጅ

የሁልጊዜ የአንተ ወዳጅ

«… በማታና በጥዋት በቀትርም እናገራለሁ እጮኽማለሁ፥ ቃሌንም ይሰማኛል» (መዝ. 55።17)።

ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነትን መገንባት በምድር ላይ ካለ ሰው ጋር ወዳጅነትን ከመገንባት ጋር ተመሳሳይ ነው። ይህ ጊዜ ይወስዳል። እውነቱ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሊሆንልህ የምትሻውን ዓይነት ቅርበት ሊኖርህ ይችላል። ነገር ግን ይህ የሚሆነው ከእርሱ ጋር ወዳጅነት ለመመስረት ፈቃደኛ ሆነህ በምትሰጠው ጊዜ ላይ የተመሠረተ ነው። ለጸሎትና ለቃሉ ጊዜ በመስጠት እርሱን ታውቀው ዘንድ አበረታታሃለሁ። በተጨማሪ ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ወዳጅነት የሚጠነክረውና የሚያድገው በመደበኛነት ከእርሱ ጋር ጊዜ ሰጥተህ በምትመላለሰው ምልልስና የእርሱን ታማኝነት በምትለማመደው ልክ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ግንኙነት እንደ ወዳጅ የምትገነባውና ከሰዎች ጋር ያለህን ጋር ያለህን ግንኙነት ከምትገነባው ጋር ያለው ልዩነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ፍጻሜው እንደ ፍጹም ወዳጅነት ነው። እርሱ ፈጽሞ አይተውህም፤ እርሱ ታማኝ፣ አስተማማኝ አፍቃሪና ይቅር ባይ ነው።

ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት ላይ እና በምታደርጋቸው ወሳኝ ነገሮች ሁሉ ውስጥ ሁልጊዜ እርሱን አሰታፊ አድርጎ መጋበዝ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። በሃሳብህ ውስጥ፣ በንግግርህ ውስጥና በየቀኑ ባለህ ሁሉም እንቅስቃሴ ላይ እርሱን ማካተት አለብህ። ችግር ሲገጥምህና ተስፋ ስትቆርጥ ብቻ ወደ እርሱ አትቅረብ። በንግድህ ሥፍራ፣ ዕቃ ስትሸምት፣ መኪና እየነዳህ፣ ጸጉርህን እያበጠርህ እያለህ፣ ከውሻህ ጋር በመዝናናት ላይ እያለህ፣ ወይም እራት ምግብ ስትሠራ ከእርሱ ጋር ተነጋገር። እርሱን እንደ አጋርና ወዳጅ ቅረበው ከእርሱ ውጪ አንድንም ነገር ማድረግን መተው አለብህ። እርሱ በእውነት በህይወትህ ተሳታፊ መሆን ይፈልጋል።

ብዙ ሰዎች እንደሚያደርጉት እግዚአብሔርን በእሁድ ጧት ሳጥን ውስጥ አታስቀምጠው። እንዲያውም ሰኞህን፣ ማክሰኞህን፣ ረቡዕህን፣ ሐሙስህን፣ ዓርብህን፣ ቅዳሜህንና እሁድህን ሁሉ ጭምር እንዲቆጣጠረው ፍቀድለት። እርሱ በኃይማኖታዊ ሥፍራ ውስጥ ብቻ ለመጠበቅ አትሞክር። ምክንያቱም እርሱ በእያንዳንዱ የህይወትህ ክፍል ውስጥ ነጻ ሥፍራ ይሻልና እርሱ የአንተ ወዳጅ መሆንን ይፈልጋል።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር ያንተ ጌታ ነው፤ በተጨማሪም እርሱ ያንተ ወዳጅ መሆን ይፈልጋል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon