የለውጥ ጊዜ

እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ቤት የጌታን ክብር እንደመስታውት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያንን መልክ እንመስል ዘንድ አክብሮ ወደ ክብር እንለወጣለን፡፡ 2ኛ ቆሮ. 3 18

የዛሬው ጥቅስ የሚያስተምረን የእግዚአብሔር ቃልና የእግዚአብሔር መንፈስ ሁለቱም በሕይወታችን በመሥራት እግዚአብሔር የሚፈልገው የሕይወት ልምምድ ውስጥ በማለፍ ለውጥን በሕይወታችን ለማምጣት ነው፡፡

ማንም ወደ ክርስቶስ የመጣ ሁሉ በሕይወቱ ለውጥ ይፈልጋል፡፡ እኛ በፍጹም ቀድሞ በምናውቀው የመረዳት ደረጃ መቆየት አንፈልግም እንፈልጋለን ታዲያ; እኛ ለውጥን እንፈልጋለን ደግሞም መፈለግ አለብን፡፡ ነገር ግን እኛ በራሳችን መለወጥ እንደማንችል መረዳት አለብን፡፡ ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ላይ በመደገፍ እርሱ እርሱ ስለሚፈልገው ለውጥና በሕይወታችን እንዲያመጣ መፍቀድ አለብን፡፡ እንደ አማኞች እኛ በፍፁም እርሱ በሕይወታችን ከሚሠራው ሥራ ጋር መተባበር አለብን፡፡ ብዙውን ጊዜ እርሱ በሕይወታችን ከሚሠራው ሥራ ጋር መተባበር አለብን፡፡ ብዙውን ጊዜ እርሱ በሕይወታችን ሊያመጣ የፈለገውን ለውጥ ስለሚነግረን የእርሱን ድምፅ ለመሥማት ልባችንን በፈቃደኝነት ለመስማት ፍላጎት ማሳያነትና አብረን ለመለወጥ መስራት አለብን፡፡ እርሱ እኛን ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ክብር ይለውጠናል፡፡

እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት እየሠራ እያለ አንደኛው መንገድ ከእግዚአብሔር የምንሰማበት መንገድ ለእርሱ የማመች ከሆነና እኛ የምንሠራው ሥራ እርሱን ከሕይወታችን ያርቃል፡፡ በማንኛውም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የእኛን ባሕሪ መለወጥ ስለሆነ ሁሉ ነገራችን ለእርሱ በማስረከብ እንዲሠራን መፍቀድ አለብን፡፡ እንግዲህ እንዲህ እንበል፡- ‹‹ጌታ ሆይ የአንተ ፈቃድ ይሁን የእኔ አይደለም፡፡››


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንቴ፡- በሕይወትህ የሚያስፈልገውን ለውጥ እንዲመጣ ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ተደገፍ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon