የሌሎች ሰዎችን ሀቀኝነት አድንቅ

የሌሎች ሰዎችን ሀቀኝነት አድንቅ

ብረት ብረትን እንደሚስል፣ ሰዉም ሌላዉን ሰዉ እንደዚሁ ይስለዋል፡፡ – ምሳሌ 27:17

ሉም ሰዉ መመስገን ይፈልጋል ነገር ግን ገንቢ ሂስ እንዴት መቀበል እንዳለባቸዉ የሚያዉቁት ጥቂቶች ናቸዉ፡፡ ማንም መሳሳት አይወድም ይህም ሰዎች ድካማችንን እና መስማት የማንፈልገዉን ነገር ሊነግሩን ሲያስቡ ከባድ ያደርግባቸዋል፡፡

ነገር ግን ስለ ሌሎች ሰዎች ሀቀኝነት አመስጋኞች መሆን አለብን፡፡ አንድ ጊዜ አንዱ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ስለ እናንተ እዉነቱን የሚነግሩአችሁ ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸዉ፤ በእናንተ የተቆጡ ሰዎች እና እጅግ የሚወዷችሁ ሰዎች ብቻ” እግዚአብሔር ሁለቱንም ዓይነት ሰዎች በሕወታችን ይጠቀቀማቸዋል፡፡ ሀቀኛ ጓደኞቻችንና የሚወዱንን ግን በልዩነት ይጠቀማቸዋል፡፡

አንድ ሰዉ ሲወዳችሁ እንዴት መሻሻል እንደምትችሉ በሐቀኝነት ይነግራችኋል፣ ዉጤቱ ከምንምና ራስን ከማንቆለጳጰስ እጅግ የተሸለና የሚጠቅም ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ብረት ብረትን ይስለዋል” የሚለዉ እንዲህ ዓይነቱን ግንኙነት ነዉ፡፡

መስማት የማትፈልጉትም እንኳ ቢሆን ስለ እናንተ እዉነቱን ስለሚነግሯችሁ ሰዎች አመስጋኞች እንድትሆኑ አበረታታችኋለሁ፡፡

እዉነቱን ስትሰሙ በተለይም ያልተገነዘባችሁትን ነገር ስትሰሙ ያለጥርጥር ሐቀኝነት የተሻለ ሰዉ ያደርጋችኋል፡፡ 


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! የእዉነት ሐቀኛ የሆኑ ሰዎችን በሕይወቴ ስላመጣህ አመሰግንሃለሁ፤ ሐቀኝነታቸዉ ምቾት የሚነሳኝ ጊዜ ይኖር ይሆናል ነገር ግን እነርሱን ሳደምጥ የተሸልኩ ሰዉ እንድሆን እንደምትረዳኝ አወዉቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon