የልመና መንፈስ

የልመና መንፈስ

በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል። (ዘካርያስ 12:10)

በዛሬዉ ቃል እንደምናየዉ፣መንፈስ ቅዱስ የልመና መንፈስ ነዉ፡፡ ይህን ስንል የፀሎት መንፈስ ነዉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የጸሎትን መሻት በዉስጣችን ያመጣል፣ እሱ የሚናገረንም በዚሁ መንገድ ነዉ፡፡ ምናልባትም ብዙ ጊዜ እንዴት ወደ ጸሎት እንደሚመራን ላንገነዘብ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር እንድንጸልይ ሲፈልግ ለመረዳት ጊዜ ይወስድብናል፣ በእርግጥም ይህን መለማመድ ያለብኝም ነገር ነዉ፡፡

አንድ ቀን ሰኞ ዕለት ስለማዉቀዉ አንድ መጋቢ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ በሚቀጥሉት ሶስት ቀናትም በተከታታይ ወደ አይምሮዬ ይመጣ ነበር፡፡ ዕሮብ ዕለት አንድ ቦታ ቀጠሮ ስለነበረኝ ሄጄ በዚያ ቦታ ጸሀፊዉን አገኘኋትና እንዴት እንደ ሆነ ጠየኳት፡፡ በዚያ ሳምንት መጋቢዉም ታሞ እንደነበረና የእሱ አባት ደግሞ የካንሰር በሽታ በሰዉነቱ ዉስጥ እንደተሰራጨ የሰማበት ጊዜ እንደሆነ ነገረችኝ፡፡

መጋቢዉ ለምን በዚያ ሳምንት ወደ ልቤ ሲመጣ እንደነበረ ወዲያዉኑ ተረዳሁ፡፡ ዝም ብዬ አስታወስኩት እንጂ እንዳልጸለይኩለት ማመን አለብኝ፡፡ በእርግጥ፣ የእግዚአበብሔርን ድምጽ መስማት ባልችልም እግዚአብሔር ለሱ የሚጸልይ ሰዉ እንዳስነሳለት እኔን ደግሞ ድምጹን መስማት እያለማመደኝ እንደነበር አምናለሁ፡፡

እንደዚህ አይነት ሁኔታ በህይወታችን ሲገጥመን፣የምንማረበት ነዉ እንጂ፤ ልንከሰስ አይገባም፡፡ የልመና ምንፈስ ከእኛ ጋር ይኖራል፣ ይመራናል እንዲሁም ይናገረናል፡፡ የእሱን ምሪት መስማትን ልናድገበትና ልንለማመደዉ የሚገባን ነገር ነዉ፡፡ ይህ ሲሆን እግዚአብሔርእንድንጸልይላቸዉ በጠየቀን ሰዎች ህይወት ታላቅ ነገርን ሲያደርግ ማየት
እንችላለን፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ ስለአንድ ሰዉ ማሰብ ብቻ ሳይሆን ብንጸልይለት የተሸለ ነገር ነዉ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon