የመንፈስን ሕይወት መኖር

የመንፈስን ሕይወት መኖር

«… እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም» (ሮሜ 8፡9)።

እኛ የተጠራነው በመንፈስ እንድንመላለስ ነው ወይም እንደዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደሚናገረው «የመንፈስ ህይወት» ለመኖር ነው። ይህንን ለማድረግ ውሳኔ መወሰን የሁሉም ነገር መነሻ ነጥብ ነው፤ ነገር ግን ከምትወስደው ውሳኔ በላይ ከእግዚአብሔር ቃልና ከልምምዴ ልነግርህ የምችለው በህይወታችን የሚገለጠው የመንፈስ ቅዱስ የጠለቀ ሥራ ይወስደናል።እርሱ መንፈስንና ነፍስን በሚለይ በእግዚአብሔር ቃል በእኛ ውስጥ «ይሰራል»(ዕብ.4፡12)። እርሱ ሁኔታዎችን በመጠቀም ለመረጋጋትና ሁል ጊዜ በፍቅር ለመመላለስ እንድንችል ያሰለጥነናል።

እኛ እንድናደርጋቸው የተጠራንበት እነዚህ ነገሮች እነዚህ በቀላሉ የጠሰጡን ነገሮች አይደሉም፤ እነዚህ በእኛ ውስጥ የሚሠሩ ናቸው። ይህ እንደ እርሾ በሊጥ ውስጥ ሠርቶ እንደሚያቦካው ክርስቶስም በእኛ ውስጥ ሥራውን ይሠራል።

በፊል 2፡12 ሐዋሪያው ጳውሎስ መዳናችንን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ እንድንፈጽም ያስተምረናል። ይህም ማለት መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን «ለእኔነት መሞት» የሚለውን የመስቀል ሥራ በእና ውስት እንደጀመረ ከእርሱ ጋር መተባባር ማለት ነው። ጳውሎስ እንደሚለው «በየቀኑ እንሞታለን»
(1ኛ ቆሮ. 15፡3)። በሌላ በኩል እርሱ እያለ ያለው በቋሚነት
«ለስጋ ሥራ መሞት» ማጋለጥ እንደሚገባ ይናገራል። በዚህ ሥፍራ እየተናገረ ያለው ስለስጋ ሞት አይደለም፣ ነገር ግን ለራስ ፈቃድና መንገድ መሞት ማለት ነው።

እውነተኛውን የመንፈስ ህይወት መኖር የምንፈልግ ከሆነ ለራሳችን ፈቃድና መንገድ ሞተን የእግዚአበሔርን ፈቃድ መምረጥ ይገባናል። እግዚአብሔር እንደሚመራንና እኛ ለእርሱ ለመታዘዝ እንደምንፈልግ ሊቆጥረን እንደሚችል መቁጠር እንችላለን።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ለራስህ እኔነት ብትሞት ለሌሎች ህይወትን የምታገለግል መሆን ትችላለህ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon