የመንፈስ ቅዱስ ኃይል

‹‹…ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ›› (የሐዋ. 1፡8)።

የእግዚአብሔር መንፈስ ድምጹን ለመስማትና እርሱን ለማገልገል ለሚፈልጉ ኃይልን ይሰጣል፡፡ አንድ ሰው አንድ ነገር ለማድረግ ፈልጎ ያንን ነገር የሚያደርግበትን ኃይል ካጣ (ከጎደለው) ይህንን ኃይል በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሊያገኝ ይችላል፡፡

ምናልባት የምታስተውል ከሆነ ኢየሱስ በውሃ ተጠምቆ ነበር፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስም ተጠምቆ ነበር፤ በሌላ በኩል እርሱ በኃይል ተሞልቶ ነበር፡፡ ይህም አባቱ እንዲሠራው የላከውን ሥራ ዘንድ የሚያስችል ነበር፡፡ የሐዋ 10፡38 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ … እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና››፡፡

ኢየሱስ የአደባባይ አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት በመንፈስ ቅዱስና በኃይል ተቀብቶ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ስንሞላ የእግዚአብሔርን ድምጽ ጥርት (በትክክል) ባለ ውስጥ ለማገልገል እንጠመቃለን፡፡ ምክንያቱ እኛ ወደ መንፈስ ቅዱስ ኃይል (ብቃት፣ ችሎታና ኃይል) በመቅረብ እርሱ በእኛ ላይ በመጣ ጊዜ ስለ እርስ ለመመስከር ኃይል እንቀበላለን፡፡ ይህ ኃይል እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚፈልገውን እንድናደርግ ያስችለናል፡፡

ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እስኪሞላ ምንም ዓይነት ተዓምራትና ኃይለና ሥራ እንዳልሠራ መመልከት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ኢየሱስ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ካስፈለገው እኛንም በእርግጠኝነት ያስፈልገናል፡፡ ዛሬና ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይሞላህ ዘንድ ጸልይ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ የመብራቱን ብርሃን ለማብራት እድሉን አለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon