ልጆች ሆይ፣ እራሳችሁን ከጣዖታት (ከሐሰተኛ አማልክት) ጠብቁ – [በልባችሁ ለእግዚአብሔር የሚገባውን የመጀመሪያ ስፍራ ከሚይዝ ከማንኛውም እና ከእያንዳንዱ ነገር ደግሞም በእግዚአብሔር ምትክ በህይወታችሁ ውስጥ የመጀመሪያውን ስፍራ ከሚይዙ ነገሮች ሁሉ] ። (1 ዮሐ. 5:21)
ከእግዚአብሔር ለመስማት እንደሚፈልግ ሰው በህይወትህ ውስጥ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሥፍራ መስጠቱ በጣም አስፈላጊ ነው። ለእግዚአብሔር ያለን መሻት ለሌሎች ነገሮች ካለን መሻት እስኪበልጥ ድረስ፣ ዲያብሎስ በእኛ ላይ የበላይነት ይኖረዋል። አንዴ እውነትን ከተረዳን የበላይነቱን ያጣ እና ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት እና ህብረት ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት በሚያስችል ሁኔታ ላይ እንገኛለን። በመጨረሻ እኛ የሚያስፈልገን እግዚአብሔር ሊሰጠን የሚችለው ነገር ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ለመማር ብዙዎቻችን ብዙ ጊዜ ይወስድብናል።
እግዚአብሔርን ለመፈለግ እና ከሌሎች ጣዖታት ሁሉ ለመራቅ ትጉህ ከሆንክ እርሱን እያከበርክ ነው እርሱም ያከብርሃል። እርሱ ራሱን ለአንተ ይገልጣል ደግሞም በፍጹም ባላሰብካቸው መንገዶች ይባርክሃል። በሕይወትህ ውስጥ ከእግዚአብሔር የምታስቀድመው ማንኛውም ነገር ወይም ማንኛውም ሰው ካለ ከልብ ራስህን ጠይቅ። ተገኝተውብህ ከሆነ ያንን በቀላሉ እግዚአብሔርን ይቅር እንዲልህ ጠይቅ፤ ደግሞም ቅድሚያ በምትሰጣቸው ነገሮች ላይ ማስተካከያ አድርግ። እሱ ቁጥር አንድ ቅድሚያ የምንሰጠው ሲሆን የሚገባውን ሥፍራ እስክንሰጠው ድረስ ሌላው ምንም ነገር አይስተካከልም።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ በህይወትህ ውስጥ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሥፍራ ስጥ