‹‹ … ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል›› (ማቴ.6፡33) ።
እግዚአብሔር የመንግስቱን ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ እንድንፈልግ ይፈልጋል (ሮሜ14፡17))፡፡ እርሱ ለትክክለኛ ባህርያትን እንድንፈልግና በትጋት የምንሰራውን ማድረግ እንድንችልና ይህንን ስናደርግ በምንፈልጋቸውና በምንሻቸው ነገሮች እርሱ በተስፋ ቃል መሠረት ሊደርግልን ይፈልጋል፡፡ እርሱ እንድንፈልገው ያፈልጋልና ይህን ስናደርግ እርሱ ሊባርከን ደስ ይለዋል፡፡
አንድን ነገር ከፈልግን እግዚአብሔር እንደሰጠን መለመንና እርሱን ሙሉ በሙሉ መታመን ይጠበቅብናል፡፡ ይሁንም እንጂ ነገሮችን ከመጎምጀት መጠበቅ ይገባናል፡፡ አንድን ነገር ከመጠን በላይ የምንፈልግ ከሆነና ያለእርሱ ደስተኛ መሆን እንደማንችል እንደሚሰማን አምናለሁ፡፡ አንድ ጊዜ አንዲት ሴትዬ እንዲህ አለችኝ እግዚአብሔር ልጅ ስላሰጣት ደስተኛ መሆን እንደማትችል ነገረችን፡፡አንድንም ብቸቻዋን የምትኖር ሴትዬም ለማግባት ባላት ፍላጎት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ አስተያየት ሰጠችኝ፡፡ እንዲህ ዓይነት አመለካከት ስህተትና እግዚአብሔርንም የሚስቆጣ ነው፡፡ ማንኛውንም ቢኖረኝ ከእግዚአብሔር ጎን ለጎን ደስተኛ ሊደርገኝ ይችላል የምንላቸውን ነገሮች ጠላት ምናልባት እኛን ሊያጠቃ ሊጠቀምበት ይችላልና ስለዚህ ፍላጎቶቻችንን በሚዛናዊነት መያዛችንን ማረጋገጥ አለብን፡፡
መጸለይ በጣም የተሻለ ነገር ነውና ነገሮች ለአንተ ለራስህ ሊሆኑልህ ሲሉ አስረው ሊያስቀሩህ ከሚሞክሩት በላይ እግዚአብሔር እንዲዘጋጅልህ ፍቀድለት፡፡ ሁልጊዜ ልትዘነጋው የማይገባ ነገር እግዚአብሔር መልካም ነውና እርሱ ለአንተ መልካም እንዲሆንልህ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዓይንህን በእርሱ ላይና በመንግስቱ ላይ አድርግ፤ እንዲሁም ለአንተ ባዘጋጀው ትክክለኛ ነገር እየተመለከትክህ ወደ ፊት ተራመድ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ማንኛውም ቢኖረኝ ደስተኛ ያደርገኛል ያልከው ነገር ምነልባት ዲያቢሎስ አንተን ሊያጠቃ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡