የሚያውኩንን ነገሮች ማስወገድ

ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሀለች፤መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሀለች፡፡ – ኢሳ 26፡9

እግዚአብሔርን ድምጽ አጥፍተው ወደ ህይወታችን ጀርባ የሚገፉ ብዙ ነገሮች በአለም አሉ፡፡እነዚህ የሚያሰናክሉን ነገሮች ከቲቪ እስከ ራዲዮ፣ ከምግብ እስከ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ በተለያዩ መንገዶች ሊመጡ ይችላሉ፡፡አንዳንዴ እንደውም የቤተ ክርስቲያን ልምምዶች ከጌታ ሊያሸሹን ይችላሉ፡፡

ነገር ግን ለእያንዳንዱ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ብቻውን የሚቀርበት ቀን ይመጣል፡፡በህይወት ያለን ማናቸውም ነገር ያልፍና እግዚአብሔር ብቻ ይቀራል፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ በሮሜ 1፡19-21 ላይ ሲናገር ስለ እግዚአብሔር የሚታወቀውን ሁሉ ራሱ በሰው ልጅ የውስጥ ህሊና ገልጧል፡፡ አንድ ቀን እያንዳንዱ ሰው ስለራሱ ህይወት በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ መልስ እንደሚሰጥ ሮሜ 14፡12 ይናገራል፡፡

ሰዎች በህይወታቸው እግዚአብሔርን ማገልገል ሳይፈልጉ ሲቀሩና በራሳቸው መንገድ መሄድን ሲፈልጉ ሊያናግራቸው እና ሊሄዱበት ስለሚገባው መንገድ ሊመራቸው ስለሚፈልገው ፈጣሪያቸው ያላቸውን ውስጣዊ ዕውቀት የሚደበቁበትን እና ችላ የሚሉበትን መንገዶች ይፈልጋሉ፡፡

ከእርሱ ጋር ህብረት ከማድረግ እና አብሮ ከመሆን ውጪ የውስጣችንን እግዚአብሔርን መሻት ሊያረካው የሚችል ነገር የለም፡፡ኢሳያስ ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሀለች፤መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሀለች…-ኢሳ 26፡9 ብሎ ሲጽፍ ለእግዚአብሔር ያለንን ርሀብ በሚገባ ገልጾታል፡፡

በህይወታችን ያለውን ዘላለማዊ ዕቅድ ለማጣጣም እግዚአብሔርን መስማት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡እግዚአብሔርን መስማት የእኛ ውሳኔ ነው ሌላ ሰው ሊሰማልን አይችልም፡፡እግዚአብሔር ፈቃዱን እንድንመርጥ ባያስገድደንም ለመንገዶቹ እሺ እንድንል ለማበረታታት ግን ሁሉንም ነገር ያደርጋል፡፡

እግዚአብሔርን ከመስማት እያሰናከላችሁ ያለው ምንድነው? ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት? ስራ? መጥፎ ልምድ? እግዚአብሔር እየተናገረ ነው፣ከእናንተ ጋር ህብረት ማድረግን ይሻል፡፡የሚያሰናክሏችሁን ነገሮች አስወግዳችሁ ተቀላቀሉት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ልክ እንደ ኢሳያስ ነፍሴ ትጠማሀለች፡፡ከምንም ነገር በላይ ድምጽህን መስማት እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡የሚደናቅፉኝን ነገር ሳስወግድ ከእኔ ጋር ለመገናኘት ታማኝ ስለምትሆን አመሰግናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon