የሚገጥምህን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችልህን ኀይል ፈልግ

የሚገጥምህን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችልህን ኀይል ፈልግ

ደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፡፡ – ሉቃ 17፡1

ወደ ፈተና መግባት ከግዜ ጅማሮ እስከዛሬ የዘለቀ የህይወታችን አካል ነዉ፡፡ ብንወድም ባንወድም ሁላችንም ከእሱ ጋር እንጋፈጣለን፡፡ በሉቃስ 17፡1 ላይ ኢየሱስ ፈተና መምጣቱ አይቀርም ብሏል፡፡

ለምንድነዉ ከፈተና ጋር የምንጋፈጠዉ? ምክንያቱም ፈተና እምነታችንን ወይም መንፈሳዊ ጡንቻዎቻችንን ስለሚያጠነክረዉ ነዉ፡፡ ፈተናን ተጋፍጠን ካልቆምን የራሳችንን መንፈሳዊ ጥንካሬ አናዉቀዉም፡፡ መንፈሳዊ ጥንካሬአችንን ለማሳደግ በሁሉም ዓይነት ፈተና በከባዱም በቀላሉም ማለፍ አለብን፡፡

በሉቃ 4 ላይ ሰይጣን የኢየሱስን ድክመት ለመጠቀም ፈልጎ እንደፈተነዉ እንመለከታለን፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ጠንክሮ ቆሞ ጠላትን ድል ነስቷል፡፡ አየሱስ በተፈተነ ጊዜ ያደረገዉ እንድታደርግ አበረታታሃለሁ፡፡ እርሱ ያደረገዉ ወደ እግዚአብሔር ቃል መጥቀስ ነበር፡፡ ኢየሱስ በፈተና እንደሚያልፍና ለእኛ ትምህርት እንደሚሆን እንደእርሱ እኛም እንደምናሸነፍ እግዚአብሄር ቀድሞ ያዉቅ ነበር፡፡ እኛ የኢየሱስን ምሳሌነት ከተከተልን ፈተናዎችን ድል መንሳት እንችላለን፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! የጠላትን ፈተና እንድቋቋምና እንዳሸንፍ ስለምትረዳኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ፈተና ሲመጣብኝ ወደ ቃልህ እሄድና በቃልህ እዉነት ድል እነሰዋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon