የማንን ድምፅ እየሰማህ ነህ?

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ሰውነታችሁን እግዚአብሔን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፡፡ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው፡፡ ሮሜ 12 1

የዛሬውን ጥቅስ ለመተግበር የተፈጥሮ ችሎታችንና ያለንን ሁሉ ለጌታችን ለመስጠት መምረጥን ይጠይቃል፡፡ በሌላ አነጋገር ለእርሱ ሰውነታችንን፣ አእምሮአችንን፣ ችሎታችንን እና ስሜቶቻችንን መስጠት ይጠይቃል፡፡ አእምሮአችንን ሰይጣን እንዳይጠቀም መጠንቀቅ አለብን፡፡ የሰው አእምሮ በጣም ምቹ የሆነ የጦርነት መሠረት ስለሆነ ቀኑን ሁሉ የሃሣብ እሳት እያቀጣጠለ ይውላል፡፡ ያንን ሃሳብ ለማድመጥ ከመረጥን የእግዚአብሔርን ድምፅ ከሕይወታችን እያወረደ ከውስጣችን ያወጣል፡፡ ሰይጣን ወደ እኛ የሚልከው ሃሣብ ብዙውን ጊዜ የሚያታልል፣ ብልጠት ያለው እና አሳሳች ስለሆነ ተታለን በቀላሉ በጉዳዩ አምነን እንቀበላለን፡፡ ሰላማችንን ለመስረቅ በመዋሸት፣ በመክሰስና ማንኛውንም ያሰበውን ውሸት ሁሉ ይነግረናል፡፡ ሰላማችንን በመዝረፍ እንድንሸማቀቅ፣ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን በማድረግና ተገቢ ያልሆነ ነገር እንድናደርግ ይገፋፋናል፡፡ የእኛን አእምሮ በክህደት ሃሣቦችና ለጆሮ በማይመች ሃሣብ ስለሌሎች ሰዎች ይሞላብናል፡፡ በእኛ መንገድ ላይ ሃሣቦችን እንዳይልክ መከልከል አንችልም፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ ኃይል መቋቋምና መቃወም እንችላለን፡፡ ከዚያ በጥንቃቄ ሃሣቦችንና እርሱ የሚናገረውን ወደ እግዚአብሔር መመለስ እንችላለን፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ አንዳንድ ጊዜ ከመጠን ያለፈ ትካዜ መጥቶ ነገሩን ወይም ሃሣቡን እስካቀነባብረው ድረስ ብዙ ጊዜ ይወስድብኛል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን! ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡ አንተም ልታደርገው ትችላለህ፡፡ በዚህ መልኩ አስባለሁ ሁለት ድምፆች የአንተን ሃሣብና ፈቃድ ለመቆጣጠር ይሽቀዳደማሉ፡፡ በአንዱ ወይም በሌላኛው ላይ ትኩረት ማድረግ ትችላለህ፡፡ እኔ ግን እግዚአብሔር የምለውን ድምፅ ምረጥ እልሃለሁ፡፡ ነገር ግን የእርሱ ያልሆነውን የጣላትን ድምፅ አትምረጥ፡፡ ሃሣባችንን በትክክለኛ ነገሮች ስንሞላ የስህተት ሃሣቦች ማረፊያ ቦታ ያጣሉ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- አእምሮህን ለእግዚአብሔር ሃሣብ በመስጠት እርሱ በሚናገርህ ሃሣቦች ላይ አተኩር፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon