ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና፡፡ – ሉቃ 1፡37
አዎንታዊ በሆነ መንገድ የሚያስቡ ሰዎች በጣም ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንኳ አቅምን ማየት ሲችሉ አሉታዊ በሆነ መንገድ የሚያስቡ ሰዎች ደግሞ ችግሮችን እና ውስንነትን ለመጠቆም ፈጣን ናቸው፡፡
አንድን ብርጭቆ ግማሽ ይዟል ከማለት እና ግማሹ ባዶ ነው ከሚለው ምሳሌያዊ ገለጻ የሚያልፍ እና በአዎንታዊ ወይም በአሉታዊ አስተሳሰብ ላይ ተመርኩዞ ውሳኔዎችን እስከመወሰን እና እርምጃዎችን እስከመሄድ የሚደርስ ነው፡፡
አሉታዊ አስተሳሰብ እንዴት ነገሮችን ከመስመር ውጪ አድርጎ እንደሚያበላሽ አስተውላችሁ ታውቃላችሁ?ችግሮች ከሆኑት በላይ ገዝፈው እና ከብደው መታየት ይጀምራሉ፡፡
አንዳንዴ በተፈጥሮ ችግር የማይቻል ሊሆን ይችላል፡፡ታዲያ አሉታዊ በሆነ መንገድ የተቃኘ አዕምሮ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ ይረሳዋል፡፡
የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰል ከአሉታዊነት ያወጣችሁና በእግዚአብሔር ማንነት ላይ እንደገና እንድታተኩሩ ይረዳችኋል፡፡በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተደገፈ አዎንታዊ አስተሳሰብ ለእግዚአብሔር የማይቻል ምንም ነገር እንደሌለ ያውቃል፡፡እሱ ሁሌም አለ፡፡
አዕምሮዬን እግዚአብሔርን እና ቃሉን እንዲያምን አሰልጥኜዋለሁ፡፡እናም ከሁኔታዎቼ በላይ እሱን ሳምነው በእግዚአብሔር በኩል የተወሰነልኝን ሀይል ተለማምጄዋለሁ፡፡ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ ማስታወስ አለብን፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ “ከባዶ ግማሽ ብርጭቆ” አስተሳሰብ ምንም የማተርፈው ነገር እንደሌለ ለእኔ ግልጽ ነው፡፡በማይቻል ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ አንተ እንዳለህ አውቃለሁ፡፡በቃልህ ስኖር የነገሮችን አዎንታዊ ጎን ማየትን መርጫለሁ፡፡