አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። – ፊልጵስዩስ 4፡19
አንዱ ሰዎች የሚገጥማቸዉ ትልቁ ፍርሃት የማጣት ፍርሃት ነዉ፡፡ ፍላጎቶቼ አይሟሉም ፣ ጥሪት አጣለሁ ፣ እግዚአብሔር በጊዜዉ አይመጣም የሚል ፍርሃት ነዉ የማጣት ፍርሃት፡፡
መሰረታዊ ፍላጎቶችህንና ሌሎች ቁሶችን ለማሟላት ተስፋ አስቆራጭ እና ከዚህ በፊት ገጥሞህ በማያዉቅ ዓይነት እጥረት ዉስት ልትሆን ትችላለህ፤ ምንአልባትም መንፈሳዊ ወይም ስሜታዊ እጥረት ዉስጥም ትገኝ ይሆናል። እግዚአብሔር አስፈልጎቶችህን አያሟላልህም ከዚህ ሁኔታ አትወጣም እያለ የፍርሃት መንፈስ እያጠቃህ ሊሆንም ይችላል፡፡
እግዚአብሔር ስለአንተ ሁኔታ ግድ እንደሚለዉና ጠላት ውሸታም እንደሆነ ዛሬ ልታዉቅ ይገባል፡፡ አንተ ምንና በየትኛዉ ጊዜ እንደሚያስፈልግህ ሊሰጥህ እየሰራ ነዉ፡፡ ምንም እየመጣ እንዳልሆነ በሚመስልም ሁኔታ እግዚአብሔር እንዴት ተዓምራዊ ሥራ እንደሚሰራ ያዉቃል፡፡
ፍላጎትህ ምንም ይሁን ምን፤ የገንዘብ፤ አካላዊ፣ ስሜታዊ፣ መንፈሳዊ ማጣት ልትፈራ አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሔር ያቀርብልሃል፣ ያጽናናሃል፣ ይመግብሃል ወደ ቀድሞውም ጥንካሬህ ያመጣሃል፡፡ በአቅርቦቱ እመን፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! አንተ ፍላጎቶቼን በሙሉ እንደምታቀርብልኝ ቃልህ ይናገራል፡፡ ስለዚህ የማጣት ፍርሃት ዉስጥ መግባት አልፈልግም፡፡ እንደምትወደኝና እንደምታቀርብልኝ አምናለሁ፡፡