የምበልጠውን ተጠባበቅ

የምበልጠውን ተጠባበቅ

የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፣ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም፡፡ ዮሐ 16 ÷ 12

ኢየሱስ የዛሬውን የጥቅስ ቃል የተናገረው ለደቀመዛሙርቱ ነው፡፡ በመሠረቱ እንዳነግራቸው እነርሱ እርሱ ልነግራቸው የምፈልገውን ለመስማት ዝግጁ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራቸው ተስፋ ገባላቸው፡፡ (ዮሐ 16÷13 ተመልከት) ኢየሱስ ይህንን ቃል ስናገር ለሦስት ዓመታት አብሮአቸው ለቆየ ሰዎች ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት ከእርሱ ጋር አብሮ ነበሩ፡፡ እሱ የሚያመለክታቸው ገና ብዙ የሚያስተምራቸው እንዳለው ነበር፡፡ እየሱስ ለሦስት ዓመታት አብሮን ብቆይ ቀንና ሌሊት ማወቅ የሚገባንን ነገር ሁሉ እንዳተማርን እናስባለን፡፡ እኔ እንደማስበው ያለማቋረጥ ለአንድ ወር ከሰዎች ጋር ብኖር የማውቀውን ሁሉ እነግራቸዋለሁ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ የምበልጥ እንድጠብቁ ነገራቸው፡፡ ምክንያቱም እርሱ ሁልጊዜ አዲስ ለሚገጥመን ሁኔታችን ለእኛ የሚለን አለው፡፡ የእግዚአብሔር መገለጥና ቃሉ የሚያድጉ ናቸው፡፡ በእርሱ ባደግን መጠን በፊት ያልተረዳነውን ለመረዳት እንችላለን፡፡ ምናልባት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አሠር ጊዜ ልናነብ እንችል ይሆናል፡፡ በሚቀጥለውም ጊዜ እናነበዋለን፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ቀደም ሲል የማናውቀውን አዲስ ነገር እናያለን፡፡ በየቀኑ እግዚአብሔር የምለውንና የሚገልጥልህና ትኩረት ከሰጠውና ከእርሱ ለመማር ከጠበቅህ የሆነ አዲስ ነገር ያስተምርሃል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- መንፈስ ቅዱስ በየቀኑ አዲስ ነገር እንደሚያስተምርህ ተጠባበቅ የተማርከውን እየዘገብክ ለመያዝ ሞክር፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon