በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔር ደስ ሊያሰኙት አይችሉም፡፡ – ሮሜ 8፡8
ከስሜቶቻችን ይልቅ መንፈስ ቅዱስን መከተል እንዳለብን ብዙ ተናግሬያለሁ ይሁን እንጂ ብዙ ሰዎች ስሜት እንዴት እንደሚሰራ እንኳን አይገነዘቡም፡፡
ስሜት የነፍስ አካል ነው፡፡ ነፍሳችን የአዕምሮ ፣ የፈቃድ እና ስሜት መዋቅር ናቸው፡፡ ምን እንደምንፈልግ ፣ ምን እንደምናስብ እና እንዴት እንደምናስብ ይናገራል፡፡ ከነዚህ ሶስቱ የነፍስ ይዘቶች ስሜታችን በቶሎ የሚነሳሳ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ከመንፈስ ቅዱስ የሆኑት ጥበብ እና ማስተዋል በቀላሉ በስሜታችን ጩኸት ውስጥ ይዋጣሉ፡፡
መጽሀፍ ቅዱስ ይህ የሥጋ ሕይወት እግዚአብሔርን አያስደስትም፡፡ እግዚአብሔር አይወደንም ማለት ግን አይደለም ፤ ይህ ማለት የሥጋ ባህሪያችንን አይቀበለው ወይም አይረካበትም ማለት ነው፡፡
አንድ ጊዜ አሉታዊ ስሜቶች እንዴት እንደሚሰሩ ከተረዳን ድል ልነሳቸው እንችላለን፡፡ በእግዚአብሔር ቃል እና በመገኘቱ ውስጥ የምንበታ ከሆነ ከነፍሳችን ብርታት በላይ መንፈሳችን ልናበረታው እንችላለን፡፡
ዛሬ ቃሉን አንሳ እና ለመንፈስ ብርታት ለስሜት ሽንፈት አድርግ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ስሜቴ በነፍሴ ላይ እንዲሰለጥን አልፈቅድም፡፡ ካንተ ጋር ጊዜን ስወስድ እና ቃልህን ሳነብ ከስሜቴ ይልቅ በመንፈስህ የምመራበትን ኃይል አስታጥቀኝ፡፡