አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ። – መዝ 3፡3
እግዚአብሔር ለህይወትህ መልካም እቅድ አለዉ ህይወትህን እንድታጣጥምም ይፈልጋል፡፡በድካም፣ በድብርትና በተስፋ መቁረጥ መንፈስ እንድትኖር አይፈልግም፡፡ መልካሙ ዜና እግዚአብሔርን ስታየዉና ከፍ እንዲያደርግህ ስትፈቅድለት አስተሳሰብህና አመለካከትህ ይለወጣል፡፡
መዝሙረኛዉ ያለዉ፤ እግዚአብሔር መጠጊያዬ ክብሬና ራሴንም ከፍ የሚያደርግ ነዉ፤ ነዉ፡፡ ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገዉ የሚለዉን ሐረግ አስብ፡፡ አንዳንድ ሰዎች አንገታቸዉን አቀርቅረዉ ሲራመዱ ስናይ እንዳዘኑ እንገምታለን፡፡ እንደዛ ከሆነ የምታስበዉ ዛሬ ይህንን እወቅ እግዚአብሔር ራስህንና መንፈስህን ከፍ ያደርጋል፡፡
አስታዉስ፡ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን መልካም ዕቅድና ተስፋ አለዉ፡፡ እርሱ ከእኛ ጋር ስላለ ከፈቃዱ ጋር በመስማማት ማሰብና መናገር እንችላለን፡፡ በሁሉም ነገር አዉንታዊ መሆንን መለማመድ እንችላለን፡፡ በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ከባድ እና ፈታኝ ሲሆኑ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ በሰጠን ተስፋ መሰረት መልካምን ነገር እንደሚያመጣ ልንተማመን እንችላለን፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ክብሬና ራሴንም ከፍ የምታደርግ ነህ፤ አንተን ለመመልከት መርጬአለሁ፡፡ ዛሬም በህይወቴ መልካም ዕቅድህን እንደምታመጣ እንዳምንህና በአንተ ላይ እንዳተኩር እርዳኝ፡፡