ማንም ሀብት እያለው፣ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ባይራራለት፣የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በእርሱ ይኖራል? – 1 ኛ ዮሀ 3፡17-18
እንደ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ርህራሄን በእያንዳንዳችን ውስጥ አስቀምጧል ለመቀበል ልባችንን የመዝጋት እና የመክፈት ውሳኔው ግን የእኛ ነው፡፡ የርህራሄ ልቤን ክፍት የሚያደርገው አንዱ ነገር ዛሬ በአለማችን ላይ ያሉትን አስፈላጊ መሰረታዊ ነገሮችን በቁም ነገር ማሰብ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
ሀሳባችንን ከእኛ ይልቅ ብዙ ወደሚጎላቸው ልናዞር እና በስቃይ ላይ ላሉት ልባችንን ልንከፍት ይገባል፡፡
1 ኛ ዮሀንስ 3፡17-18ን አንብቡ፡፡ ይህንን ቃል በጣም ነው የምወደው ምክንያቱም አስረግጦ ጉድለትን አይቼ እንደ ሌላ ሰው ሀላፊነት በመቁጠር ማለፍ እንደሌለብኝ ይጠቁመኛል፡፡ ወይም እውነት ያልሆነውን ጉድለቱ እጅግ ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ እኔ ምንም ማድረግ እንደማልችል እንዳላስብ ይነግረኛል፡፡ ስለ አንድ ሁኔታ እኔ እና እናንተ ሁሉንም ነገር ማድረግ ባንችል እንኳ የሆነ ነገር ግን ማድረግ እንደምንችል በአገልግሎታችን አይቻለሁ፡፡ ይሄ ልናደርገው የምንችለው ነገር ደግሞ ለሰዎች ተስፋን መስጠት ነው፡፡
የርህራሄ ልባችሁን በአለም ዙሪያ ተስፋ አስቆራጭ ጉድለቶች ላሉባቸው አስፍታችሁ ለመክፈት እንድትፈቅዱ እጸልያለሁ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ በራስ ወዳድነት የሌሎችን ጉድለት ረስቼ መኖር አልፈልግም፡፡ ሌሎችን እረዳ ዘንድ የአንተን ርህራሄ ለመቀበል ልቤን እከፍታለሁ፡፡