የቃል ኪዳን ምድርህን ለመዉረስ ቁልፉ

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።ኤፌ 2:10

ግዚአብሔር ወደ ቃል-ኪዳኑ ምድር ሊመራህ ይፈልጋል… በክርስቶስ ዳግም ከተፈጠርህ፤ ከተወለድህ በኋላ ለአንተ የታቀደዉን መልካም ህይወት መኖር ትችል ዘንድ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን ወደዛ ህይወት መከተልህ ከመጀመርህ በፊት ሊያዘጋጅህ ይፈልጋል ስለዚህ የተወሰኑ ነገሮች መቀየር አለባቸው ማለት ነዉ፡፡

ለዉጥ የሚለዉን ቃል አትፍራ፤ በቃ በቀላሉ ለዉጥ ማለት ከዚህ በፊት የምትሰራዉን ነገር ቀይረህ አዲስ ሳታደርገው የነበረን ነገር ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ አሉታዊ ነገር ማሰብ አቁምና አዉንታዊ ነገር ማሰብ ጀምር፤ በምቾት ቀጠና መኖር አቁምና ከዛ ቦታ መውጣት፤ ጊዜህን ማጥፋት አቁምና እድሎችን ተጠቀም፡፡

ስለ ተስፋይቱ ምድር ማንበብና ማወቅ ብቻዉን በቂ አይደለም፡፡ የተስፋ ምድርህን ለመዉረስ ወስን፡፡ እግዚአብሔር መልካም ነዉ ወደዚያ ይመራሃል፡፡ እግዚአብሔር ለሌሎች በረከት ሊያደርግህ ወደ ህይወትህ የሚያመጣዉን ለዉጥ ለማስተናገድ ለመቀበል ፈቃደኛ ሁን፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ የተስፋይቱን ምድር መዉረስ እፈልጋለሁና ለዉጡን አሳየኝ፡፡ ለእኔ ያለህን ዓለማ ለማሟላትና ለሌሎች በረከት ልታደርገኝ እያዘጋጀሀኝ ስለሆነ አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon