የቅናት አደጋ

የቅናት አደጋ

ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። – ያዕ 3፡16

ቅናት የሚፈጥረዉ ቁጣ መጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ቀድመዉ ከተጠቀሱት አሉታዊ ስሜቶች አንዱ ነዉ፡፡ ዘፍ 4 የሚነግረን ቃይል ወንድሙን አቤልን የገደለዉ በቅናት ተቆጥቶ ነዉ፡፡ ይህ አንዱ የቅናት የመጨረሻዉ ዉጤት ነዉ፤ ቅናት እንዴት አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ያስታዉሰናል፡፡

ዛሬ ብዙ ሰዎች የማንነታቸዉ ዋጋ ወይም የእነርሱ ጥቅም በስራቸዉ፣ በማህበራዊ ተደማጭነታቸዉ ወይም በቤተ ክርስቲያን ባላቸዉ ቦታ የሚወሰን አድርገዉ ያስባሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ አንድ ሰዉ በላያቸዉ ሲሾም ያፍራሉ። ቅናት በሰዉ ፊት አስፈላጊ እንደሆኑ እንዲቆጠር ሙከራ እንዲያደርጉ ያደርጋቸዋል፡፡

በዚህ ዓይነት አመለካከት እየታገልህ ከሆነ እግዚአብሔር ባለህበት ቦታ ለምክንያት እንዳስቀመጠህ ተረዳ፡፡ እርሱ ለህይወትህ መልካም ዕቅድ አለዉ እንዴት መዘጋጀት እንዳለብህም እርሱ ያዉቃል፡፡

የትንንሽ ጅማሮ ቀናትን አትናቃቸዉ፡፡ ደስታችንና ሙላታችን የሚመጣዉ እግዚአብሔር በህይወታችን ያስቀመጠዉን ግልጽ ጥሪ በመታዘዝ እንጂ ነገሮችን በማሳካት ሰዎችን ለማስደመም በምናደርገዉ ሙከራ አይደለም፡፡ ቅናት በዉስጥህ እንዲያድግ አትፍቀድ፡፡ መገኘት ያለህበት ቦታ ላይ እንዲያደርግህ እግዚአብሔርን እመን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ቅናት አገደኛ ነዉ ፣ በሕይወቴ ስፍራ እንዲኖረዉ አልፈልግም፡፡ ተቀባይነት በምድራዊ ስሌትና እዉቅና መደገፍ የለበትም፤ እኔ የምፈልገዉ አንተን ነዉ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon