የብቸኝነት ስሜት ሳይሰማዎት ብቻዎን መሆን ይችላሉ

የብቸኝነት ስሜት ሳይሰማዎት ብቻዎን መሆን ይችላሉ

በርቱ ፣ አትፍሩ ፣ በእነሱ ፊት አትደንግጡ ፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሄዳል አለው። እሱ አይጥልህም ወይም አይተውህም። – ኦሪት ዘዳግም 31:6

አንዳንዴ ብቸኝነትን፣ ባዶነትን ወይም ደግሞ ፍቅርን የመፈለግ ውስጣዊ ህመም የምንለማመድበት ጊዜ አለ፡፡ የዚህ ዓይነቱ ተጽዕኖ ደግሞ የባዶነት፤ ከንቱነትና ዓላማ ቢስነት ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ለብቸኝነት በርካት ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ ነገር ግን ብዙ ሰዎች በዚህ መንገድ መኖር እንደሌለባቸው አይረዱም፡፡ ሊቃወሙትና ሊቋቋሙት ይችላሉ፡፡

ብቻህን ስለሆንክ ብቻ ብቸኛ መሆን አለብህ ማለት አለመሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ምንም እንኳ ሁል ጊዜ ብቸኛ መሆንን ማስወገድ የማይቻል ቢሆንም ከብቸኝነት ተጽዕኖ ራሳችንን የምንጠብቅበት መንገድ ግን አለ።

እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ስለሆነ ጠንካራና ደፋር እንድንሆን የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል፡፡ በአካል ብቻህን ልትሆን ትችላለህ ያ ማለት ግን ብቸኛ መሆን አለብህ ማለት አይደለም ምክንያቱም እግዚአብሔር ሁልጊዜ በመንፈስ ካንተ ጋር ነው፡፡ እርሱም በፍጹም አይተውህም ፤ አይረሳህምም፡፡

ሌላ ጊዜ የብቸኝነት መንፈስ በህይወትህ ሲመጣብህ ዘዳግም 31፡6 ን እንድታስታውስ አበረታታሃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደሆነ ጮክ ብለህ አውጅ ፣ እርሱንም ማነጋገር ጀምር፡፡ ለእርሱ ክፍት ስትሆንና ስፍራ ስትሰጠው የእርሱ መገኘት/ህልውና ሕይወትህን ይሞላል፡፡ በሄድክበት ሁሉ የእግዚአብሔር ህልውና ከአንተ ጋር እያለ ብቸኛ መሆን የለብህም፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አንተ ሁል ጊዜ ከእኔ ጋር ስላለህ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ አንተ ከእኔ ጎን/ አጠገብ ሆነህ ብቸኝነት ሊሰማኝ እንደማይገባ አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon