የተለየሕይወት

የተለየሕይወት

«አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ» (መዝ.25፡1)።

በዛሬው እለት በመረጥነው ጥቅስ ላይ እንደምንመለከተው በማለዳ እጆቼን ወደ ላይ በማንሳትና የመሰጠትን ጸሎት መጸለይን እወዳለሁ፡፡ እንዲህ ብዬም ‹‹አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ›› እናገራለሁ፡፡ ይህ መሰጠት የሚለው ቃል ትክክለኛው ትርጉም ሙሉነትን፣ በፈቃደኝነት ራስን ለጌታ እጅ መስጠት ወይም መማረክን የሚያመላክት ነው፡ በመሰጠት ጸሎት ለእርሱ እንዲህ ትላለህ « እግዚአብሔር ሆይ አሁን በፊትህ ነኝ ራሴን ለአንተ እሰጣለሁ፣ ገንዘቤን ሳይሆን ነገር ግን ራሴን፣ በእሁድ ማለዳ አንድ ሰዓት ሳይሆን ነገር ግን ራሴን፣ የቀኔን የተወሰነ ጊዜ ሳይሆን ነገር ግን እኔን እራሴን፣ ጌታ ሆይ ሁለንተናዬን ለአንተ አቀርባለሁፀ በአንተ ፊት ራሴን አስቀምጣለሁ፤ በእኔ ልታደርግ የምትፈልገውን ነገር አድርግ፣ ዛሬ በእኔም ተናገር፣ ሰዎችን በእኔ አልፈህ ዛሬ ወደ ህይወታቸው ድረስ፣ ዛሬ በእኔ በቀናቶቼ ላይ ልዩነትን ፍጠር፣ እኔ የሁሉም ነገር ባለቤት ሳልሆን ባለአደራ ነኝ። ዛሬ ሁለንተናዬንና ያሉኝ ሁሉም ነገሮች የመጡት ካንተ ናቸውና ላንተው አሳልፌ እሰጣለሁ።»

አንድን ነገር ለእግዚአብሔር ስንቀድስ ወይም ስንሰጥ ይህ ነገር እግዚአብሔር እንዲጠቀምበት ለእርሱ መለየታችን ነው። ስለዚህ ህይወታችንን ለእግዚአብሔር ስንቀድስ ወይም ስንሰጥ ለሥጋዊ ምኞቶች፣ ለምድራዊ እሴቶች፣ ለሥጋዊ አስተሳሰቦች፣ ላልተገራ አኗኗር፣ ለመጥፎ ልማዶችና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ለማይስማሙ ማንኛውም ነገሮች ሁሉ ጀርባችንን መስጠታች ነው። በዓለም ላለው ጩኸት ጆሮአችንን ዘግተን ለእግዚአብሔር ድምጽ ክፍት እናደርጋለን። እንዲህ ስናደርግ በዓላማ ራሳችንን ከዓለማዊ ነገሮች እናርቃለን፣ እንዲሁም ደግሞ እግዚአብሔር እንዲጠቀምብን ራሳችንን እናዘጋጃለን እንዲሁም እናቀርባለን። ራስን መቀደስ ውም መስጠት ማለት ቀላል ነገር አይደለም፣ ነገር ግን መሰጠት ለሚፈልገው የተገራ (ዲሲፕሊን ላለው)ና ለመስዋዕትነት ህይወት የተገባ ነው።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ለእግዚአብሔር እንዲህ በል « ዛሬ እነሆ»።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon