የተረጋጋ፣ዝግ ያለ እና ቋሚ ያለው ህይወት የመኖር ነጻነት

የተረጋጋ፣ዝግ ያለ እና ቋሚ ያለው ህይወት የመኖር ነጻነት

አንተ ግን በሁኔታዎች ሁሉ የረጋህ ሁን፤መከራን ታገስ፤የወንጌል ሰባኪን ተግባር አከናውን፤አገልግሎትህን ፈጽም፡፡ – 2 ኛ ጢሞ 4፡5

ሰዎች የተወለዱት ነጻ ሆነው ለመኖር ነው፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው። ጥያቄው ነጻ ለመሆን ማለፍ በሚገባችሁ ሁሉ ለማለፍ ፈቃደኛ ናችሁ ወይስ ቀሪውን እድሜያችሁን በሙሉ ባላችሁበት መቀጠል ነው የምትፈልጉት? የሚለው ነው፡፡ ነጻ መሆን ከፈለጋችሁ ቁልፉ እግዚአብሔር እንድታደርጉ የሚፈልገውን ማድረግ መጀመር ነው፡፡ በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ እየተራመዳችሁ ቀስ በቀስ ከችግሮቻችሁ ትወጣላችሁ፡፡

በ2ኛ ጢሞ.4፡5 ላይ ጳውሎስ ጢሞቲዎስን በሁኔታዎች ሁሉ የረጋህ ሁን ፤ መከራን ታገስ ፤ የወንጌል ሰባኪን ተግባር አከናውን ፤ አገልግሎትህን ፈጽም ብሎ ይነግረዋል፡፡ ይሄ ለእኛ መልካም ምክር ነው፡፡

በስሜቶቻችን በመመራት ፋንታ ችግሮች ሲያጋጥሙን ረጋ ብለን እግዚአብሔር እንድናደርግ የጠራንን ነገር ማድረግ ላይ ማተኮር አለብን፡፡ በሆነ ነገር ከተናደዳችሁ ፣ ህይወታችሁን እንዲያፈርስ ከመፍቀድ ይልቅ ለመልካም ነገር ጠይቁት፡፡ ለጎዷችሁ እና ጥቃት ላደረሱባችሁ ሰዎች በመጸለይ ክፋትን እና ንዴትን አሸንፉ፡፡ ለሌላ ሰው መልካም በማድረግ የራስ ወዳድነትን ስሜት መልሳችሁ ተቋቋሙት፡፡

መቼም ጠላት ስሜታችሁን ሊበጠብጠው ሲፈልግ ተረጋጉና እግዚአብሔር እንድታደርጉ የጠራችሁን አድርጉ!


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ህይወቴን በነጻነት እንድደሰትበት እና እንድሰራው የጠራኸኝን ስራ እንድሰራ ረጋ እና ዝግ እንድንል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon