‹‹… እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል›› (ኤፌ. 1፡14)።
መንፈስ ቅዱስ ሊመጣ ላለው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ዋስትና የተሠጠን ዋስትናችን (ቀብዳችን) ነው፡፡ እኔ ብዙውን ጊዜ፤ በተለይም በመንፈስ ቅዱስ እንደተሞላሁ በእውነት ሲሰማኝ እንዲህ እላለሁ ‹‹ይህ እጅግ መልካም ነው፤ ሊመጣ ያለው ፍጹም የሆነው የክብር ሙላት ምን እንደሚመስል ለመገመት አልችልም›› አሁን እኛ ከሚመጣውና ልንወርሰው ከተገባን ሙላት እንኳን አስር በመቶውን (ይህ የተለመደ የቀብድ ክፍያ ነው) የተለማመድን ቢሆን እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ስንመለከተው የሚሆነው ምን ሊሆን እንደሚችል ስናስብ፤ በዚያ ልቅሶ የለም፣ ሀዘን የለም፣ ሞት የለም፡፡ እነዚህ ሀሳቦች በሙላት በመገረም እንደምንመለከተው ያደርገናል፡፡
በኤፌ.2፡13 -14 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው እኛ በመንፈስ ቅዱስ እንደታተምን ይናገራል፣ እናም በሰላም ያለ ችግር እንደምንደርስና ከሚመጣው ሁሉ ጥፋት እንደምንተርፍ ዋስትና ሰጥቶናል፡፡ ከመጨረሻው ቀን ከኃጢአትና የኃጢአት ውጤት ነጻ እንሆናልን፡፡ የዚህን አስደናቂ ነገር አንዴ አስብ! መንፈስ ቅዱ በእኛ ውስጥ አለ፣ ለመጨረሻው የእረፍት ቀን ይጠብቀናል፣ በዚያ መቃብር የለም ያለው በእግዚአብሔር ህልውና ውስት ሰማይ ብቻ ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ አሁንና በዚህ ህይወት ሳለን የሚስደንቁ ነገሮች ያደርግልናል፡፡ እርሱ ይናገረናል፣ ይመራናል፣ ይረዳናል፣ ያስተምረናል፣ ምክርን ይሰጠናል፣ በህይወታችን አስደናቂውን የእርሱን ዓላማ ለመፈጸምና ከዚም በላይ ሥራ ሊሠራ ኃይልን ያሰጠናል፡፡ በምድራዊ ህይወታችን ምንም እንኳን አስደናቂ ልምምዶችን ያለን ቢሆንም እነዚህ ሁሉ ወደ ፊት ለምናገኛቸው ነገሮች ሁሉ ቅድመ ቅምሸዎች ናቸው፡፡ የተሸለው እየመጣ ስለሆነ አሁን እኛ ቀብድ (መያዥያ) የሚሆን አለን፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ከቀብድ መያዥያ ጋር የተሰጠን ርስት እንዳለን በማወቅ የደህንነት ዋስትና ሊሰማን ይችላል፡፡