አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። – ማቴ 6፡3
ሁላችንም ሰማዕት ምን እንደሆነ እናዉቃለን፡፡ ለክርስቶስ የሞቱ ጀግና ወንዶችና ሴቶች ታሪክ እናዉቃለን፡፡ ነገር ግን የማያበረታታና ግሩም ያልሆነ ለሚሰማዉ ሁሉ ህመሙን ማካፈል የሚፈልግ ሌላ ዓነት ሰማዕት ደግሞ አለ፡፡ እነዚህ ሰማዕታት እነርሱ በህይወታቸዉ የከፈሉትን ስቃይ በዙሪያቸዉ ያለዉ ሁሉ እንዲያዉቁ ይፈልጋሉ፡፡
የ“ሰማዕትነት ወጥመድ” ለመዉደቅ ቀላል የሆነ ነገር ነዉ፡፡ ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችንን ማገልገል እንጀምራለን እንወደዋለንም፡፡ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ ልባችን መለወጥ ይጀምርና ምላሽ ይፈልጋል፡፡ ከሆነ ግዜ ቡሃላ የአገልጋይነት ልብ አይኖረንም፡፡ አመለካከታችን መራር ይሆናል ፤ በራሳችንም እንጸጸታለን፡፡ ሰማዕት ወደ መሆን እንመጣለን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ቀኝ እጃችን የምትሰጠዉን ግራችን እንዳታዉቅ ነዉ፡፡ በሌላ አባባል እግዚአብሔር የሚፈልገዉ ሰዎች እንዲያዉቁልን ወይም እንዲገነዘቡ መፈለግ ሳይሆን እንዲሁ እንድናገለግል ነዉ፡፡
በሰማዕትነት ወጥመድ ዉስጥ ወድቀሃል? ከሆነ እዉቅናን ሳትፈልግ ያለስስት ራስህን እንድትሰጥ እግዚአብሔር ልቡን እንዲሰጥህ ጠይቀዉ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
መንፈስ ቅዱስ ሆይ በሰማዕትነት ወጥመድ ወድቄ እንደሆነ አሳየኝ፤ ሌሎችን ራሴን ሰጥቼና በደስታ ማገልገል እንድችል የአንተን ልብ እፈልጋለሁ።