እርሱ ለቅኖች ደኀንነትን ያከማቻል፣ ያለ ነውርም ለሚሄዱት ጋሻ ነው፡፡ የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፣ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል፡፡ የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንና መልካም መንገድን ሁሉ ታስታውሳለህ፡፡ ምሳሌ 2፡7-9
በሕይወት ጎዳና ላይ መንፈሳዊ ምልክቶች አሉ፡፡በእግዚአብሔር ጥበቃ ስር ለመቆየት በእርሱ ታመን፣ አትጨነቅ አትፍራ፣ ድፍረት ይኑርህ የሚሉትን እነዚህን ምልክቶች መታዘዝ አለብህ፡፡ ለእነዚህ ምልክቶች ተገቢውን ትኩረት ከሰጠህ በመንገዱ ላይ መቀጠል ቀላል ይሆንልሃል፡፡ እግዚአብሔር ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ጥበቃ፣ ሰላምና ደስታ ትለማመዳለህ፡፡
ይሁንና እነዚህን ምልክቶች ባትታዘዝ መንገዱ በተወሰነ ደረጃ የፍጥነት መቀነሻ እንዳለው ትረዳለህ ፤ በችሎታህ የሚኖርህ ድፍረትም ከዚህ በፊት እንደነበረው አይሆንም፡፡ በየመንገዱ ስለሚገጥምህ የማይታወቁ ነገሮች የተነሳ ልትጨነቅና ከመንገዱም ውጪ ልትወጣ ትችላለህ፡፡
እግዚአብሔር መንገዳችንን ስለሚጠብቅ እኔና እናንተ ግን ልንሰጋ አይገባም፡፡ ምልክቶቹን ችላ በማለት ለምን ጊዜያችንን እናባክናለን? የሚታዘዝ ልብ ይኑራችሁ፡፡ የእርሱን ምልክት ስትመለከቱ ተከተሉት፡፡ የእርሱን ምልክት ስትከተሉ ደግሞ ፍጻሜያችሁ ላይ በሰላም ትደርሳላችሁ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ፤ በሕይወት መንገዴ ላይ ያስቀመጥክልኝን መንፈሳዊ ምልክቶች እንድመለከት እርዳኝ፡፡ ባየኋቸው ጊዜ በህይወት ዘመኔ ሁሉ እታዛቸዋለሁ፣ እከተላቸዋለሁ፡፡