የተሻለ ሐሳብ ምረጥ የተሸሻለ ህይወት ያዝ

የተሻለ ሐሳብ ምረጥ የተሸሻለ ህይወት ያዝ

ይህ ክፍል በግልጽ የሚናገረዉ ሞትና ሕይወት በምንናገራቸዉ ቃላት ዉስጥ እንዳሉ ነዉ፡፡ አንደበታችንን መቆጣጠር መለማመድ አለብን ግን ደግሞ በትክክለኛዉ መንገድ ስለማድረጋችን እርግጠኞች መሆን አለብን፡፡

እኔ እንደማስበዉ አንዳንድ ሰዎች አንደበታቸዉን ለመቆጣጠር ይጥራሉ ሀሳባቸዉን በተመለከተ ግን ምንም አያደርጉም፡፡ ይህ ልክ የአረምን ጫፍ ይዞ እንደመንቀል ነዉ፣ ሥሩ እስካልተነቀለ ድረስ ድጋሚ መብቀሉ አይቀርም፡፡ በቅድሚያ አእምሮህን ካልተቆጣጠርክ አንደበትህን መቆጣጠር ፈጽሞ አትችልም፡፡

ዘወትር መጥፎ ነገሮችን በማሰብ እንፈተናለን ግና መቀበል የለብንም፡፡ ምርጫ አለን! ትክክል እንድንናገር ትክክል የሆነዉን አስተሳሰብ በዓላማ መምረጥ እንችላለን፡፡

ከእግዚአብሔርና ከቃሉ በመስማት፣ በማንበብ ፣ በማሰብና በመናገር ሕይወት ሰጪ አስተሳሰብ መምረጥ ትችላለህ፡፡ ዉስጥህ ያለዉ ነገር ነዉ ውጪ የሚወጣበትን መንገድ የሚፈልገዉ፡፡ ስለዚህ አእምሮህን በመልካም፣ በአዉንታዊ፣ በሐይለኛ፣ በሕይወት ሰጪ ነገሮች ስትሞላ አዉንታዊ፣ ሐይለኛ፣ ሕይወት ሰጪ ቃላት በተፈጥሮ ይከተላሉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ሕይወት ሰጪ ቃላትን እናገር ዘንድ አስተሳሰቤን መለወጥ እፈልጋለሁ፡፡ ቃሎቼ ቃሎችህን እንዲያንጸባርቁ አእምሮዬን አድስ፤ እርዳኝም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon