ዳሩ ግን፣ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱን ሁኑ ተብሎ ስለተፃፈ፣ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፡፡ – 1ኛ ጴጥ 1፡15
እየኖርን ካለነው ኑሮ በበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን አስባለሁ፡፡ ይህ ሲባል በፍርሃት እስክንኖር ድረስ እንድንጨናነቅ ወይም ልክ ነኝ አይደለውም በሚል በህግ እንድንታሰር አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔራዊ በሆነ መንገድ እንድንጠነቀቅ ነው፡፡
ወዳጃችን ማን ሊሆን እንደሚገባ፣ ምን ዓይነት የቴሌቪዥን ፕሮግራምና ፊልም ማየት እንዳለብን፣ ምን ዓይነት መፅሐፍ ማንበብ እንዳለብን፣ ምን ዓይነት ሙዚቃ ማዳመጥ እንደሚገባ፣ ገንዘባችንን እንዴት መጠቀም እንዳለብን እና ጊዜያችንን ምን ላይ ማዋል እንዳለብን ካልተጠነቀቅን የባከነ ህይወት ኖረን እናልፋለን፡፡
እንደክርስቲያን ቅድስናን መፈለግ እና መስዋዕት እንደሆንን መገንዘብ አለብን፤ ይህም ማለት እግዚአብሔር እንዲጠቀምብን ተለይተናል ማለት ነው፡፡ በእርግጥም፣ ልክ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛችን በተቀበልንበት ቅስፈት በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰን እግዚአብሔር ላዘጋጀው ዓላማ ተለይተናል፡፡ ይህንን ዓላማችንን ካላሳካን ወይም ይህን ዓላማችንን ያለማቋረጥ ተከታትለን ለመኖር ካልፈለግነው፣ ባዶነትና ተስፋ መቁረጥ ይሰማናል፡፡
ዛሬ የመቀደስ ዓላማችሁን እንድትፈልጉት አሳስባችኋለሁ፡፡ አስቸጋሪ የሆኑ ከባድ ውሳኔ የሚጠይቁ ሁኔታዎች ሊያጋጥማችሁ ይችላሉ፣ በዚህ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ለእናንተ ያዘጋጀውን የቅድስናን መንገድ ምረጡ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ኢየሱስ ሆይ! ከቅድስና ህይወት የሚያርቀኝን ማንኛውንም ነገር ለይቼ እንዳውቅ እርዳኝ፡፡ በአንተ እገዛ በጥንቃቄ በመኖር፣ ለእኔ ያዘጋጀኸውን የቅድስና የህይወት መንገድን መከተል እፈልጋለሁ፡፡