የተቀደሱ፣ የተገረዙ ጆሮዎች

የተቀደሱ፣ የተገረዙ ጆሮዎች

ለማን [እኔ ኤርሚያስ] ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማኛል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣ መስማት አይችሉም። በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤ ደስም አይሰኙበትም። (ኤርምያስ 6:10)

እግዚአብሔር በተናገረ ቁጥር እና እርሱን እንዳልሰማውነው በሆንን ቁጥር እርሱን ለመስማት እጅግ አስቸጋሪ ወደሚሆንበት ደረጃ እስክንደርስ ድረስ ልባችን ይደነድናል። በመጨረሻም፣ ግትርነታችን እርሱን በጭራሽ የመስማት አቅማችንን ያዳክማል። መልካም እንደሆነ በገባን ነገር ላይ ጀርባችንን በዞርን ቁጥር እግዚአብሔር ለእኛ በሚናገረን በጣም ብዙ ጊዜ እና እሱን የማንሰማው ያህል የምንሰራ ከሆነ እርሱን ለመስማት እጅግ አስቸጋሪ ወደሆነ ደረጃ እስክንደርስ ድረስ ልባችን ትንሽ ይቀራል።

በዛሬው ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ኤርምያስ ስለ ሕዝቡ መጥፋት እንዲያስጠነቅቅ እንደፈለገ እንመለከታለን፤ ነገር ግን ጆሯቸው ያልተገረዙ (ከእግዚአብሔር ጋር ባለመሆናቸው) የተነሳ ድምፁን መስማት አልቻሉም። እንዴት አሳዛኝ ነው!

በአንጻሩ፣ በዮሐንስ 5፡30 ላይ ኢየሱስ የተቀደሰ (የተለየ)፣ የተገረዘ ጆሮ እንዳለው እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔርን ከመስማት ጋር በተያያዘ ይህ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ጥቅሶች አንዱ እንደሆነ አምናለሁ-“በራሴ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም [ያለጥገኝነት፥ በፈቃዴ – ግን እግዚአብሔር እንደተናገረኝ እና የእርሱን ትዕዛዝ ብቻ ነው]። እንደሰማሁ እንኳ እንዲሁ እፈርዳለሁ
[ውሳኔ እንድወስን እንደተጋበዝኩ እወስናለሁ። ድምፁ ወደ እኔ እንደመጣ፣ እንዲሁ እወስናለሁ] ፣ እናም የእኔ ውሳኔ ትክክል (ትክክለኛ፣ ጻድቅ) ነው፣ ምክንያቱም የራሴን ፈቃዴን አልፈልግም ወይም አልመክርም (ለራሴ የሚያስደስት ነገር ለማድረግ ፍላጎት የለኝም፥ ለገዛ ዓላማዬ፥ ለገዛ እቅዴ) ። ነገር ግን የላከኝን የአብን ፈቃድ እና ደስታ ማድረግ ብቻ ነው።”

ኢየሱስ የአባቱን ድምፅ ካልሰማ በስተቀር ስለአንድ ጉዳይ ምንም አላደረገም። የእግዚአብሔርን ምክር ካለመፈለጋችን የተነሳ ከገባን በኋላ እንዲታደገን እርሱን ከምንፈልግበት ምስቅልቅል ህይወት ከመግባታችን አስቀድመን የእግዚአብሔርን ምክር ጠይቀን ቢሆን ኖሮ ህይወታችን እንዴት የተለየ ሊሆን እንደሚችል እስቲ አስቡት።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ውሳኔ ከመወሰንህ በፊት ልብህን አድምጥ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon