የነቃና የቀና ሕልውና ይኑርህ

የነቃና የቀና ሕልውና ይኑርህ

መንፈስ ግን በግልጥ በኃይለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን ትምህርት እያደመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ፡፡ በገዛ ሕልውናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው …. 1 ጢሞ 4፡ 1-2

የዛሬው ጥቅስ የሚያወራው የሰው ሕልውና ሊደነዝዝ እንደሚችል ነው፡፡ ቁስል ሲመረቅዝና ሌሎች ሲሞቱ ምንም የሕመም ስሜት ያጣል፡፡ ልክ እንደዚሁ የሰው ሕልውና ሲጎዳና ሲደነዝዝ ስሜት የለሽና ደንታ ቢስ ይሆናል፡፡ ለአመታት የግል ቁስልና ያለመታዘዝ ችግር ያለባቸው ሰዎች አስቸጋሪና ትህትና ያጡ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፀጋ ውስጥ ስንሆን መለወጥ ይቻላል፡፡ በእግዚአብሔር ፊት በቆየን መጠን ሕልውናችን የነቃ ስለሚሆን ሌሎችን ስንጎዳም ሆነ እግዚአብሔርን ሳንታዘዝ ስንቀር ወዲያው ሊታወቅን ይጀምራል፡፡

እግዚአብሔር የትህትና ልብንና የነቃ ሕልውና እንዲሰጥህ ከለመንክ ስለ እርሱ እና ከእርሱ ጋር ባለህ ጉዳይ ንቁ ትሆናለህ፡፡ በሕይወታቸው ለአመታት ካላቸው ችግር የተነሣ የማይታዘዙ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎች ስታገኝ ስለእነርሱ ፀልይ፡፡ ጥሩ ስሜት በማይሰማንና ጌታን በማያስከብር ሁኔታ ውስጥ ሆነን ስሜታችንን እረፍት በሚያጣበት ወቅት ቶሎ ብለን ከሁኔታው መለየት መልካም ነው፡፡

በየጊዜው መንፈስ ቅዱስ ሕልውናህ እንዲነቃ ለሚያደርገው ጥረት እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ እግዚአብሔር ለምህረቱ እያመሰገን፣ ቶሎ የባሕሪይ ለውጥ ለማምጣት እንድንችል እንዲረዳን እንፀልይ፡፡ ኦባ፡ ስለ እራሴና ስለምወዳቸው ወገኖቼ የልብ ድንዳኔና የሕሊና መደንዘዝ ምህረትና ፈውስ እለምናለሁ፡፡ ትህትናና፣ የነቃ ሕሊና፣ ለአንተ ድምፅና ምረት ቶሎ ብለን ምላሽ ለመስጠት እንድንችል እርዳን፡፡ አንተ እንድናደርግ ለምትፈልግ ምላሽ ለመስጠት እንድንችል በኢየሱስ ስም እርዳን አሜን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ለውሳኔ አቋም ይኑርህ፣ በልብህ ቅን ሁን!!

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon