የአንተን “ማ?” ካንተ “ሥራ” ለይ

የአንተን “ማ?” ካንተ “ሥራ” ለይ

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። – 2 ቆሮ 5፡17

እኔ በህይወቴ ስህተት ሰርቼ አዉቃለሁ ወደ ፊትም ስህተት እንደምሰራ እርግጠኛ ነኝ ነገር ግን አሁንም ራሴን እወደዋለሁ፡፡ እዉነታዉ እኔ ሁል ጊዜ ትክክል ላላደርግ እችላለሁ ይህ ማለት ግን በክርስቶስ ማን መሆኔን አይነካዉም፡፡ እንደተወደድኩና አሁንም መልካም ሰዉ እንደሆንኩ አዉቃለሁ፡፡ ይህም የሆነዉ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ስለሆንኩ ነዉ፡፡ ሥራዬን ከማንነቴ መለየት ተምሬአለሁ፡፡

ያደረግከዉን ነገር ስታስብ ማን መሆንህን አትወስን፤ ከሀፍረት ነጻ የሆነ አዲስ ነጻነት መለማመድ ትችላለህ፡፡ እግዚአብሔር እንደወደደህ ስታስተዉል ራስህን ጤናማና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መዉደድ ትጀምራለህ፡፡ ራስህን መዉደድ ስትጀምር ሌሎች ሰዎችም አንተን መዉደድ ይጀምራሉ፡፡ ራስን መዉደድ ማለት በትዕቢት መሞላት ማለት አይደለም በቀላሉ እግዚአብሔር አንተ እንድትሆን የፈጠረህን ማንነት መቀበል ማለት ነዉ፡፡

ሁላችንም በባህርያችን ለዉጥ እንፈልጋለን ነገር ግን እግዚአብሔር እንደፈጠረን ራሳችንን መቀበል በስሜታችን ጤናማ እንድንሆንና ለዉጥ እንድናመጣ ወሳኝ ነገር ነዉ፡፡ ራሳችንን መዉደድን ብንችልበት ሀፍረትን መሰረት ያደረገን ተፈጥሮ እንድናሸንፍ ያግዘናል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ሥራዬን ከ ማንነቴ መለየት እንድችል እርዳኝ፤ አንተ ስለወደድከኝና በሕይወቴ በቋሚነት ስለምትሰራ ራሴን መዉደድ እችላለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon