የአጨራረስ ጠቀሜታ

የሰጠኸኝን ስራ በመፈጸም በምድር አከበርሁህ፡፡ – ዮሐ 17፡4

ብዙ አመታት በፊት በጌታ ፊት ያስለቀሰኝን አንድ ቃል አነበብኩ፡፡በዮሐንስ 17፡4 ላይ ኢየሱስ የሰጠኸኝን ስራ በመፈጸም በምድር ላይ አከበርሁህ ይላል፡፡እያለ ያለው እግዚአብሔርን መከተል ማለት በእኛ ላይ ያለውን ጥሪውን መፈጸም ነው ማለት ነው ፡፡

ያንን ቃል ካነበብኩ በኋላ እግዚአብሔር የጠራኝን ጥሪ መኖር ብቻ ሳይሆን ጥሪዬን መጨረስ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ነገር ሆነ፡፡

ተነጥለው ወጥተው ከእግዚአብሔር ጋር ጉዞ የጀመሩ ሰዎች ብዙ ናቸው ነገር ግን የጨረሱት ብዙ አይመስሉኝም፡፡ሓዋሪያው ጳውሎስ በሐዋ 20፡24 ላይ …ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበልኩትን ሩጫዬን እና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም…ብሏል፡፡

በእኔ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ፈጽሜ ለመጨረስ እና እያንዳንዱን ደቂቃ እየተደሰትኩ ለማሳለፍ ቆርጫለሁ! ለእናንተም የምፈልገው ይህንኑ ነው-የህይወታችሁን እያንዳንዱን ቀን እንድትደሰቱበት እና እግዚአብሔር የጠራችሁን ጥሪ ፈጽማችሁ እንድትጨርሱ ነው፡፡

ነገር ግን የዚህ ነገር አብዛኛው ድርሻ የእኛ ነው እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡እርሱ የራሱን ድርሻ በክርስቶስ የሚያስፈልገንን ሁሉ በመስጠት ተወጥቷል፡፡በመማር፣በማደግ እና የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን እንዲሰራ በመፍቀድ መቀጠል የእኛ ድርሻ ነው፡፡እግዚአብሔር ምን ምን ነገሮችን እንድታደርጉለት እንደጠራችሁ ለማሰብ ጊዜን ውሰዱ እና ራሳችሁን እግዚአብሔር በፊቴ ያየውን በጥንካሬ ለመጨረስ ዛሬ ላይ ምን እያደረግኩ ነው? ብላችሁ ጠይቁ፡፡

እግዚአብሔር ለእናንተ ታላላቅ እቅዶች አሉት፡፡በእምነት ተቀበሏቸውና በሙሉ ልባችሁ ልትፈጽሟቸው ትጉ፡፡ዛሬ ጠንክራችሁ ለመጨረስ ውሳኔ ውስጥ እንድትገቡ እፈልጋለሁ፡፡እግዚአብሔር የሚያከብረው ውሳኔ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ልክ እንደ ኢየሱስ ለእኔ የሰጠኸኝን ስራ ጨርሻለሁ ማለት መቻል እፈልጋለሁ፡፡ለአላማህ ለመኖር ሀይል እና መሻት ለመስጠት ስራዬን በደስታ እንድጨርስ በውስጤ እየሰራህ ስላለህ አመሰግናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon