የእሳት ጥቅምት

የእሳት ጥቅምት

እኔስ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችሃለው፣ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የምመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፡፡ እርሱ በመንፈስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፣ ማቴ 3÷11

እኛ አማኞች እሁድ ጠዋት ወደ ቤተክርስቲያን (አምልኮ ሥፍራ) ከመሄድ ያለፈ ሥራ ለመሥራት ነው የተጠራን፡፡ ኃይማኖታዊ ሥራቶችንና በዓሎችን ከማክበር ያለፈ ነገር ለመሥራት ወይም የውሃ ጥምቀትን በጭንቅላታችን ከማፍሰስና ለመሥራት (ለማድረግ) ነው የተጠራነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ማከናወን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ መከተል ያለባቸው ተስፋ የተገባውን በመለማመድ መሆን አለበት፡፡ ያም ‹‹የእሳት ጥምቀት ነው፡፡›› ለያዕቆብና ለዮሐንስ እናት ልጆቿን አንዱን በቀኝ አንዱን ደግሞ በግራ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ እንዲያስቀምጥላት ለጠየቀችው ጥያቄ በሚመለስበት ጊዜ (ማቴ 20÷20-21 ተመልከት) እናንተ የምትጠይቁትን (የምትለምኑትን) አታውቁም ለመሆን እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጡ ዘንድ ትችላላችሁ; እኔ የምጠመቀውን ጥምቀትስ ትጠመቁ ዘንድ ትችላላችሁ; (ማቴ 20÷22 ተመልከት)

ስለየትኛው ጥምቀት ነው ኢየሱስ እየተናገረ ያለው; ቀደም ብሎ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ የውሃ ጥምቀት በወሰደ ጊዜ በዚያው በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቆአል (ማር 1÷9-11) ታዲያ ሌላ ምን ጥምቀት አለ;

ኢየሱስ ስለ እሳት ጥምቀት ነበር የሚናገረው እሳት የመቀደስ ተልዕኮ ነው ያለው እሱ ሥራውን ሲሰራ ምቾት አይሰጥም፡፡ ኢየሱስ ኃጥያት የለበትምና የሚቀደስ ስላለው በእሳት ሊጠመቅ አይገባም ነበር፡፡ እኛም ግን ያስፈልገናል፡፡ ኢየሱስ ነው በመንፈስ ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቀው፡፡

ኢየሱስ በእሳቱ እንዲያጠምቅህ ድፍረት ይኑርህ፡፡ እርሱ የማንጻትና የማጽዳት ሥራ በሕይወት በመሥራት እርሱን በሚጠቅም መልክ ሕይወትህን እንዲሠራው ጠይቀው፡፡ በዚያ ውስጥ ጠለፋ ሊከብድ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚያረካ ሽልማት አለው፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በእሳት ውስጥ ባለፍህ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሆናል፡፡ እርሱ አይተውህም ወይም አይጥልህም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon