የእግዚብሔር ፍቅር ስሜትን መሰረት አያደረግም

የእግዚብሔር ፍቅር ስሜትን መሰረት አያደረግም

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም፡፡ – ሮሜ 5፡5

የሰው ፍቅር እንደ እግዚአብሔር ፍቅር ያለ ቅደመ ሁኔታ ማፍቀር አይቻለውም፡፡ በኢየሱስ እንደሚያምን አማኝ የእግዚብሔር ፍቅር በውስጣችን አለ፡፡ ይህ ፍቅር ያለ ሁኔታ እንዲፈስ መፍቀድ ይገባናል፡፡ የእኛ ፍቅር ገደብ አለው ፤ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ፈጽሞ ገድም የለውም፡፡ የእኛ ፍቅር ያልቃል ፤ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ማለቂያ የለውም፡፡

አንዳዴ በራሴ ብርታት አንድን ሰው መውደድ እንደማልችል ባውቅም በእግዚአብሔር ግን ማፍቀር እችላሁ፡፡ እውነተኛው የእግዚአብሔር ፍቅር ውሳኔን እንጂ ስሜትን መሰረት አያደረግም፡፡ ሰውዬው ይገባዋል ወይስ አይገባውም በሚልም አይደለም፡፡ እናም የሚምገርም ነጻነት ነው ያለው አንድ ሰው ይገባዋል ወይም አይገባውም ሳንል ፍቅር መስጠጥ።

የሰው ፍቅር ስሜት መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የምንወዳቸው ሰዎች ለእኛ መልካም ስለሆኑልን ወይም አስቀድመው ስለወደዱን ነው፡፡ ይህን መሰል ፍቅር ይመጣል ይሄዳል፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር ፈጽሞ ልዩ ነው፡፡ በማንነቱ እንጂ ምንም ነገርን መሰረት ያደረገ አይደለም፡፡ ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል ያኔ የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ፈሰሰ፡፡ ይህንን ፍቅር ዛሬ ለሎችም አፍስሱት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ የኔ ፍቅር ያልቃል ያንተ ግን ፈጽሞ አያልቅ፡፡ አቤቱ ይገባቸዋል ወይም አይገባቸውም ሳልል ለሌሎች ይህን ፍቅር አካፍል ዘንድ በአንተ ፍቅር ውስጥ እጠልቃለሁ ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon