የእግዚአብሔርን መቅደስ በአግባቡ ጠብቁ

የእግዚአብሔርን መቅደስ በአግባቡ ጠብቁ

ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና የራሳችሁ አይደላችሁም፡፡ – 1 ቆሮንቶስ 6፡19

ስልሳ አራት ዐመት ከሞላኝ ወዲህ በቋሚነት የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴ አላደርግም ወይም በቅጡ አልያዝኩትም፡፡ በመልካም አቋም ለመሆን በትንሹ እራመዳለሁ ወይም የተወሰኑ ነገሮችን አደርጋለሁ ነገር ግን እንቅስቃሴውን ለማድረግ እራሴ አልሰጠሁም ነበር፡፡ የሰውነት ማጎልመሻን ላለማዘውተር የማልሰጠው ምክንያት የለም ፤ ነገር ግን ጌታ ጠንከር ብዬ ለሶስተኛው የሕይወቴ ምዕራፍ የሰውነት ማጎልመሻ ማዘውተር እንዳለብኝ ተናገረኝ፡፡

ጥሩ የሚባል የአመጋገብ ልማድ አልኝ ፤ ጌታን ታዝዤ በተደጋጋሚ ወደ የሰውነት ማጎልመሻ ሥፍራ መሄድ ስጀምር ወደ አዲስ የሕይወቴ ወቅት ገባሁኝ፡፡ የተሻለ ገጽታ ኖረኝ ፣ ጥሩ ተሰማኝ እንዲሁም የሰጠኝን አካል በአግባቡ በመጠበቄ እግዚአብሔርን እያከበርኩኝ ነው፡፡

በዚህ አቅጣጫ ሕይወታችሁን ለማሻሻል ዝግጁ ከሆናችሁ ጤናማ ሕይወትን ለመምራት ምን ማድረግ አለበኝ ብላችሁ በጸሎት ጠይቁ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሰውነታችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው ይላል፡፡ እግዚአብሔር የሚወደው ሰውነት እንዲኖራችሁ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ!

ዛሬ መቅደሳችሁን በአግባቡ ለመያዝ ወስኑ!


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ የበለጠ ጤናማ ሕይወት ዘይቤ እና ኑሮ መሰጠት እፈልጋለሁ፡፡ ጤናዬን እንዳሻሽል የሚያደርግ ጥሩ ምርጫዎችን እንዳደርግ እርዳኝ ፡፡ ሰውነቴ ያንተ መቅደስ ነው ፤ በአግባቡ እይዘዋለሁ፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon