የእግዚአብሔርን ሥጦታ በመለማመድ ተስፋ ተደሰት

የእግዚአብሔርን ሥጦታ በመለማመድ ተስፋ ተደሰት

በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን። – ሮሜ 5፡2

መጽሐፍ ቅዱስ ለእኔና እናንተ በተገቡና በተስፋ በተሞሉ ቃሎች የተሞላ መጽሐፍ ነዉ፡፡ ወደ እግዚአብሔር መገኘት መድረስ እንችላለን፡፡ ከበሽታዎቻችን ሊፈዉሰን ይፈልጋል፡፡ ሁሉንም ፍላጎቶቻችንን ያቀርብልናል፡፡ እጅግ ብዙ ለመቁጠር ብዙ ሌሎችም አሉ፡፡ ለዚህ ነዉ ክርስቲያኖች በእምነት ማጣት ከእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ሲጎድሉ ማየት የሚያሳዝነዉ፡፡

ጥያቄዉ ይሄ ነዉ፡ እነዚያን ተስፋዎች እየተጠባበቃችሁ ነዉን? መልካም ነገሮች መከሰት የሚጀምሩት እናንተ በተስፋዉ በቋሚነት መደሰት ስትጀምሩ ነዉ፡፡

ሉቃስ 2፡52 የሚናገረዉ ኢየሱስ በሰዉና በእግዚአብሔር ፊት በእምነት በሞገስ እንዳደገ ነዉ፡፡ እኛም በዚያ ሞገስ ማደግና እንደ ኢየሱስ ተስፋዉን መለማመድ እንችላለን፡፡ እነዚያን ነገሮች አሁን በህይወትህ እያየህ ካልሆነ እንደሚመጡ በማወቅ መደሰትና ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ መጣል ትችላለህ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ተስፋ የተገባ ነገር ሁሉ ለእኛ ነዉ፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ክብር በመለማመድ ተስፋ ተደሰት እርሱም ታላቅ ነገር በህይወትህ ያመጣል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ለእኔ ያለህን ተስፋ እየተጠባበኩ እደሰታለሁ፡፡ በቃልህ ተስፋ የተገቡልኝን ነገሮች ሁሉ እንደምታመጣልኝ አምናለሁ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon