የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥጦታ መላበስ

የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥጦታ መላበስ

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። – 2 ቆሮ 5፡21

ራስህን መጠየቅ ያለብህ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች እነዚህ ናቸው፡፡ በክርስቶስ ማን እንደሆንኩ አውቃለሁ? በጽድቅ እየተመላለስኩ ነው?
በርካታ ሰዎች እነዚህን ጥያቄዎች በትክክል መመለስ አይችሉም፡፡ ይህም እግዚአብሔር እንዲመላለሱበት በቀደላቸው የነጻነትና ሰላም ሕይወት ልክ እንዳይኖሩ ይከለክላቸዋል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ክርስቶስን እንደ አዳኝ አድርገን በተቀበልንበት ቅጽበት እግዘአብሔር ኃጢያታችንን ወስዶ የራሱን ጽድቅ ሰጥቶናል፡፡ ይህ ስጦታ እንጂ የሚገባን ደሞዝ አይደለም፡፡ ይህንን ጽድቅ ልንለብሰው ያስፈልገናል፡፡ ይንን ስናደርግ የእርሱን ሰላም እንቀበላለን፡፡

በክርስቶስ ያለንን ማንነት በምናውቅበት ጊዜ ማድረግ ያለብንን ነገር ለማድረግ ሰላምና መተማመን ይኖረናል፡፡ ክርስቶስ እንደሚወድህና ለአንተ እንደሞተልህ ስትረዳ በየዕለቱ እርሱን ለመውደድ የሚቻልህን ሁሉ ታደርጋለህ፡፡

በክርስቶስ ማንነትህን ስታውቅ የተገዛልህ ጽድቅ በመልበስ በጽድቅ መመላለስ ትችላለህ፡፡ ለአንተ ያለውን ፍቅር ስትለማመድ ያለህ ምላሽ በሁለንተናህ ሁሉ ለእርሱ መኖር ይሆናል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ ሁል ጊዜ በአንተ ማን እንደሆንኩ መገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ ያደረክልኝን ሁሉ በማስታወስ የአንተን ጽድቅ በየዕለቱ ተላብሼ እንድኖር እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon