«… በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው» (ኤር. 17፡7)።
የእግዚአብሔር ህልውና ወደ ህይወታችን የሚጋብዝ አንድ አመለካከት ከማንኛውም ነገርና ከማንም ሰው በላይ እርሱን የሚያከብር አመለካከት ነው። የእኛ አመለካከት እንዲህ ሊል ይፈልጋል/ይገባል/ «እግዚአብሔር ሆይ ማንኛውም ሰው ስለሚናገረኝ ነገር ቢኖርም፣ ስለራሴ የማስበው ነገር ቢኖርም፣ ስለራሴ የማቅደው ቢኖርም፣ አንተ የምታናግረኝን አንድ ነገር ብሰማ አንተ እንደሆነክ አውቃለሁ፣ አከብርሃለሁ፤ እንዲሁም አንተ የምትለውን ከማንኛውም ነገር በላይ አከብራለሁ»
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ከሚናገረን ይልቅ ሰዎች ለእኛ ስለሚናገሩት ነገር የበለጠ ትኩረት እንሰጣለን። አጥብቄ ብጸልይና የእግዚአብሔርን ድምጽ ብሰማ ከዚያም በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች ምን እንደሚያስቡ በመጠየቅ ብጀምር የሰዎችን አመለካከት ከእግዚአብሔር ሃሳብ በላይ እናከብራለን። ይህ ዓይነት አመለካከት የእግዚአብሔርን ድምጽ በቀጣይነት ለመስማት እንዳንችል ያደርገናል (ያቅበናል)። መቼም ቢሆን ከእግዚአብሔር የመስማት አቅም (ችሎታ) እያዳበርን የምንሄድ ከሆነ ከብዙ ሰዎች የሰዎችን አስተያየት መስማትን የምናቆምና በልባችን በሚሞላ የእግዚአብሔር ጥበብ መታመን እንጀምራለን። ከሰዎች መልካምን ምክር የምንቀበልበት ጊዜ አለ። ነገር ግን የሰዎችን ድምዳሜ ብቻ የምንፈልግ ከሆነ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ እንወጣለን።
ሰይጣን እኛ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ብቃት የሌለን ነን ብለን እንድናስብ ይፈልጋል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ይህ እውነት እንዳይደለ ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል። ምክንያቱም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በግላችን የምንመራ እንድንሆን ይፈልጋል። እርሱ እንደመራንና እንደሚያስተምረን የእርሱ ድምጽ ለራሳችን እንድንሰማ ይፈልጋል። ለዛሬ በመረጥነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ እርሱ ብቻ የምንመለከት ከሆንን እንባረካለን። በኤር 17፡5 – 6 መሠረት በተራ ወንዶችና ሴቶች በከንቱ የሚታመኑ ላይ እጅግ የከፋ ቅጣት ይመጣባቸዋል ይላል። ነገር ግን በጌታ በሚታመኑና እርሱን የሚያከብሩ ብጹአን /የተባረኩ/ ናቸው። እግዚአብሔርን የምንሰማ ከሆንን መልካም ነገር ለእኛ ይሆንልናል። እርሱ ብርታታችን ሊሆን ይፈልጋልና ከማንኛውም ነገር ሁሉ ይልቅ እርሱን ልናከብር ይገባናል።
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ሌሎች ሰዎች የሚሉትን አዳምጣቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን ግን በትክክል ስማው።