የእግዚአብሔርን ጊዜ ተቀበል

የእግዚአብሔርን ጊዜ ተቀበል

እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብፅም እንዳይመለስ ብሎአልና። ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ምድር ተሰልፈው ወጡ። – ዘጸ 13፡17-18

እግዚአብሐየር በሕይወታችን አንድ ነገር እንዲሆን ሲፈልግ ተስፋና ህልም ይሰጠናል፡፡ ነገር ግን የእርሱ ዕቅድ የሚሆንበትን ትክክለኛ ጊዜ እንድናይ አይፈቅድልንም፡፡ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም ይህንን አለማወቃችን ነው በእግዚአብሔር ፕሮግራም እንድንቀጥል የሚደርገን፡፡ የእግዚአብሔርን ጊዜ ስንቀበል እግዚአብሔር በችግሮቻችን ላይ ሲሰራ በተስፋ መኖርንና በሕይወት መደሰትን እንማራለን፡፡

ዘጸ 13፡7 ላይ እግዚብሐየር የእስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር ያደረጉትን ጉዞ በረጅሙና አስቸጋሪው መንገድ መራቸው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ወደ ተስፋይቱ ምድር ገብቶ ለመውረስ ገና እንዳልተዘጋጁ ያውቅ ስለነበር ነው፡፡ ለስልጠና የሚሆን ጊዜ ሊኖራቸው ይገባ ስለነበረ በጣም አስቸጋሪ በሆኑ አንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፍ ነበረባቸው፡፡ በእነዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ እግዚአብሔር ለእነርሱ የሚያደርገውን እንክብካቤና ማድረግ የሚፈልግውን ነገር ማድረግ አላቆመም ነበር፡፡

በእኛም ሕይወት እውነታው ተመሳሳይ ነው፡፡ በእግዚአብሔር የስልጠና ጊዜ እሱ እንድናደርግ ያዘዘንን ነገር ያለ ምንም ጥያቄና ሁሉንም ነገር ለማወቅ ሳንሞክር እንድናደርግ ይጠብቅብናል፡፡ ነገሮች ምንም ያህል ጊዜ ቢወስዱ የእግዚአብሔርን ጊዜ መጠበቅ መልካም እንደሆነ በመሉ ድፍረት እንተማመናለን፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ የአንተን ጊዜ እቀበላለሁ፡፡ ሁል ጊዜ ላልረዳው እችላለሁ፡፡ ነገር ግን የአንተ መንገዶች ፍጹም እንደሆኑ አውቃለሁ፡፡ ሙሉ በሙሉ በአንተ እተማመናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon