የእግዚአብሔርን ጥበብ ተጠባበቅ

መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል።ምሳሌ 1114

ሰዎች አዘዉትረዉ እንዲህ ይጠይቁኛል “በእግዚአብሔር እዉነት እየተጓዝኩ ይሁን በራሴ ስሜትና ፈቃድ በምን እርግጠና እሆናለሁ?” መልሱ በትዕግስት እንደሚገኝ ተስፋ አምናለሁ፡፡

ስሜቶቻችን ያስቸኩሉናል፣ አንድ ነገር እንድናደርግ ደግሞም አሁኑኑ እንዲሆን ይነግሩናል፡፡ እግዚአብሔራዊ ጥበብ ግን የሚነግረን ግልጽ እይታ እስክናገኝ ድረስ እንድንታገስ፣ ምን መቼ ማድረግ እንዳለብን እንድናስብ ነዉ፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ከመወሰናችንና ለተግባር ከመጣደፋችን በፊት ከእግዚአብሔር ጠቢብ ምሪት እና ምክር እንድንፈልግ ይነግረናል፡፡

ወደ ኋላ መመለስና ነገሮችን ከእግዚአብሔር አንጻር ልንመለከት ያስፈልጋል፡፡ በሚሰማን ሳይሆን በምናዉቀዉ ተመስርተን ዉሳኔ መወሰን ያስፈልገናል፡፡ የእርሱንና የሚታመኑ ሰዎችን ጥበብ ልንቀበል ያስፈልጋል፡፡

ከማንኛዉ ከባድ ዉሳኔ ጋር ስትፋጠጥ እንዳትጸጸት ከመወሰንህ በፊት ግልጽ መልስ እስክታገኝ ታገስ፡፡ ስሜቶች ጥሩ ናቸዉ ነገር ግን በዕዉቀትና በጥበብ ላይ የበላይነት ማግኘት የለባቸዉም፡፡ የእግዚአብሔርን ምሪት ጠይቅ ምን ማድረግ እንዳለብህም እርሱ ይንገርህ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በስሜቴ መመራትና ወደ ዉሳኔ መፍጠን አልፈልግም፡፡ ለምመርጠዉ ምርጫ የአንተን ጥበብ ለመፈለግ እፈቅዳለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon