የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀበል

የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀበል

ነገር ግን ስጦታዉ እንደበደሉ መጠን አይደለም፤ በአንድ ሰዉ መተላለፍ ብዙዎች ከሞቱ፣ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰዉ፣ ይኸዉም በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የመጣዉ ስጦታ ለብዙዎች እንዴት አብልጦ ይትረፍረፍ፡፡ – ሮሜ 5፡15

ጸጋ እግዚአብሔር አንድትሮርበት በጠራህ መንገድ እንድትኖር የሚረዳህ የእግዚአብሔር ኀይል ነዉ፡፡ ግን እግዚአብሔር ከፋቃዱ ዉጪ እንድንኖር ጸጋን አይሰጠንም፡፡ እኛ ልናደርገዉ የወሰንነዉን አንድ ነገር እንዳናደርግ እየነገረን ከሆነ ቅባቱን የማጣት ከባድ ልምምድ ይገጥመናል፡፡

ጸጋ ብቃትን ይተካከላል፡፡ እግዚአብሔር በህይወታችን ያለዉን ጥሪዉን ለመፈጸም ጸጋን ይሰጠናል፡፡ የራሳችንን ነገር ስናደርግ በራሳችን እያደረግን ነዉ፤ የእርሱን ምሪት ስንከተል ጸጋን ይሰጠናል ጥሪያችንን እንድንፈጥም ሐይልም ይሰጠናል፡፡

አስደሳቹ ነገር ጸጋዉን ለመቀበል ስንመርጥ እሱን ለማግኘት ማድረግ የሚገባን አንዳች ነገር አለመኖሩ ነዉ፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሪ ለመከተል ስትመርጥ እርሱ ሊረዳህ ዝግጁና ፈቃደኛ ነዉ፡፡ ኢየሱስ ኀጢአትህን ለመሸፈን ሞቶአል ስለዚህ በየቀኑ በህይወትህ ውስጥ የሚመራህን መንፈስ ቅዱስን አግኝተህ በእግዚአብሔር ፊት የጽድቅ ህይወት መኖር ትችላለህ፡፡

ዛሬ ጸጋዉንና ብቃቱን መቀበል የምትችልበት ቦታ ስለመሆንህ እርግጠኛ እንድትሆን አነሳሰሃለሁ፡፡ የራስህን መንገድ ለመከተል እየሞከርክ ከሆነ እግዚአብሔርን እርሱን መከተል እንደምትፈልግና አንዲረዳህ ጠይቀዉ፡፡ እርሱ ጸጋዉን ላንተ ለመስጠት ሁል ጊዜ ታማኝ ነዉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ! ያለአንተ ጸጋ በህይወቴ ስኬታማ ኑሮ መኖር አልችልም፤ ጥሪህን መከተል እፈልጋለሁ ደግሞም አንተ እንድኖር የምትፈልገዉን ህይወት በየዕለቱ እንድኖር እንድትረዳኝ እጠይቅሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon