ወዳጅ ሆይ፤ነፍስህ በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለች ሁሉ መልካም ጤንነት እንዲኖርህና በነገር ሁሉ እንዲሳካልህ እጸልያለሁ፡፡ – 3 ኛ ዮሀ 1፡2
ሁለንተናችሁ-መንፈስ ፣ ነፍስ እና ስጋችሁ-ለእግዚአብሔር እጅግ አስፈላጊና በእቅዱ ውስጥ አስፈላጊ ክፍልን የሚጫወቱ ናቸው፡፡ እያንዳንዱን ክፍል የመጠበቅ ሀላፊነትን ለእናንተ ሰጥቷችኋል፡፡ ነገር ግን በህይወታችን ልናደርግ የምንችለው በቂ የማይሆንበት ጊዜ ላይ እግዚአብሔር እርሱ ብቻ ሊያደርግ የሚችለውን እንዲያደርግ ልናምነው ይገባል፡፡
ልክ እኔ በ1980ዎቹ መጨረሻ ከጡት ካንሰር ጋር ስታገል በነበረበት ወቅት እፈልግ እንደነበረው ምናልባት አካላዊ ፈውስ ትፈልጉ ይሆናል፡፡ወይም ደግሞ ልክ በልጅነቴ ለአመታት ጥቃትን ከማስተናገዴ የተነሳ አዕምሯዊ ወይም ስሜታዊ ፈውስ እንደምፈልገው ትፈልጉ ይሆናል፡፡ ምንም ሆነ ምን እኔ እና እናንተ በሁለንተናችን ጤናን እንድንለማመድ ይፈልጋል፡፡
እኔ እና እናንተ በማናቸውም መንገድ ስንታመም እና ጤና ስናጣ እግዚአብሔር እንድናደርገው የጠራንን ነገር ከማድረግ እና በህይወት ከመደሰት ይከለክለናል፡፡ እግዚአብሔር ለእናንተ የታቀደ ትልቅ የወደፊት ሀሳብ ስላለው በስጋ ፣ ነፍስ እና መንፈስ-ጤናማ መሆን ምንም ይሁን ምን ለማድረግ የጠራችሁን ለማድረግ ዝግጁ ለመሆን አስፈላጊው ክፍል ነው፡፡ ዛሬ ለፈዋሹ ሀይሉ ጸልዩ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ስለሁሉም የህይወት ክፍሌ ስለምትጠነቀቅልኝ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በተበላሸ ማናቸውም የህይወቴ ክፍል ላይ ድንቅ የሆነውን የፈውስህን ሀይል እቀበላለሁ፡፡