መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ፡፡ 2 ጢሞ 1፡14
በብሉይ ኪዳን ዘመናት አዳምና ሔዋን በኤደን ገነት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ይገናኙ ነበር፡፡ ሙሴም ደግሞ በሲና ተራራ ላይ ይገናኘው ነበር፡፡ በዛሬ ጊዜ ግን እግዚአብሔር በጓሮአችን ወይም እቅርባችን ባለው ተራራ ላይ በምናደርገው ግብዣ ወይም ጥሪ አይደለም የምናገኘው፡፡ እርሱ ልክ የእስራኤል ሕዝብ በምድረበዳ ሲጓዝ በነበረ ጊዜ እንዳደረገው ዓይነት በድንኳን ለመኖር አይፈልግም፡፡ እንደዚሁም እርሱ የሰው እጅ በሠራው ሕንፃ ወይም ቤተመቅደስ አይኖርም፡፡
ኢየሱስን በተቀበልን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በቅፅበት በእኛ ውስጥ ለመኖር ይመጣል፡፡ (ዮሐ 14 17 ተመልከት) እግዚአብሔር በመንፈሳችን ውስጥ መኖርያ ለማድረግ መረጠ በውስጠኛው የሕይወታችን ክፍል ከማንኛውም ሕይወት ካላቸው ነገሮች በላይ ለእኛ ወደሚቀርብበት ሁኔታ ላይ መኖር ፈለገ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በልባችን ውስጥ ሲኖር የእኛ መንፈስ ለመንፈስ ቅዱስ ምቹ መኖሪያ ይሆናል፡፡ (1 ቆሮ 3 16 ተመልከት) ሕይወታችንም ከእግዚአብሔር መገኘት የተነሣ የተቀደሰ ይሆናል፡፡
እኛ አማኞች ያለንበት የተቀደሰ ሁኔታ በነፍሳችንና በሕይወታችን ውስጥ በእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን እግዚአብሔር እየሠራ እንዳለ ያረጋግጣል፡፡ በሕይወታችን ለሚያውቁን ሰዎች በሂደት የሚደረጉ ለውጦችና ክስተቶች እውነተኛ ምስክሮች ናቸው፡፡ እኛ በእርግጥ የምንመራው እንዴት ከውስጥ ወደ ውጭ እንደምንኖር ነው፡፡ እግዚአብሔር በነፍሣችን ውስጥ የሰራው የሚገርም ሥራ መንፈስ ቅዱስም ደግሞ የሚያስተምረን እንዴት አድርገን እርሱ ለሚያስፈልጋቸው ዓለም ምስክር እንድንሆን ያስተምረናል፡፡
የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከውስጥ ወደ ውጭ የሆነ ሕይወት ኑሪ፡፡