ጌታ የሰውን ውጫዊ ገጽታ አይመለከትም ፡፡ እግዚአብሔር ልብን ያያል ፡፡ – 1 ሳሙ 16፡7
የአንዳንድ ሰዎችን አለባበስ በተመለከተ በጣም ፍርድ የተሞላበት አስተሳሰብ ነበረኝ፡፡ ኮንፈረንሶች ላይ ሳስተምር ጂንስ መልበስ የለብኝም ብዬ አስብ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ልጄ “በእርግጥ እግዚአብሔር ከጂንስ ይልቅ ፖሊስተርን የበለጠ ይመርጣል ብለሽ ታስቢያለሽ?“ ብሎ ጠየቀኝ፡፡
የነበረኝን ኃይማኖታዊ አመለካከት ለማደስና ወደ ማስተዋል ተመልሼ ብዙዎችን የምደርስ እንድሆን እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነቱን የማስደንገጫ መንገድ ተጠቅሞ ነበር፡፡
በእርግጥ ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄድ በጥሩ ሁኔታ ለብሶ መሄድ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ዋናው ቁም ነገር ማተኮር ያለብን ዋና ግባችንን በመጣል ውጫዊ ገጽታችን ላይ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነትን ማሳደግ ላይ መሆን አለበት፡፡
እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ኀብረት እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡ ይህ ማለት ልክ ከቅርብ ቤተሰቦቻችንና ወዳጆቻችን ጋር እንደምናደርገው በውሏችን ሁሉ ከእርሱ ጋር ኀብረት እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ግድ የሚለው ውጫዊ ሁኔታችን ሳይሆን እውነተኛ ግንኙነት ማድረግ መቻላችን ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ጊዜ እንውሰድ፣ በሕይወታችን ለሰራው ስራና ላደረገልን ነገር አመስጋኞች እንሁን፡፡ እውነተኛ ግንኙነትና ኀብረት ይኑረን፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ውጪያዊ ነገር የአንተ አስተሳሰብ እንዲኖረኝ እርዳኝ፡፡ አለባበሳቸው እኔ ትክክል ነው በምለው መንንድ በለበሱ ሰዎች ላይ እንዳልፈርድ እርዳኝ፡፡ ከአንተ ጋር ጠንካራ የሆነ ውስጣዊ ኅብረት እንዳዳብር እርዳኝ፡፡