የእግዚአብሔር ቃል መልካም መድሀኒት ነው

የእግዚአብሔር ቃል መልካም መድሀኒት ነው

ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው፡፡ – መዝ 107፡20

ብዙዎች የእግዚአብሔርን መድሀኒት ማለትም ቃሉን መውሰድን ስለ ፈውስ ባላቸው መረዳት የመተካት ስህተትን ይፈጽማሉ፡፡ ቃሉን ሳይጠቀሙ ወይም ተግባራዊ ሳያደርጉ ”በፈውስ አምናለሁ” ይላሉ፡፡ ካልወሰድነው መድሀኒት እንዴት ሊረዳን ይችላል?

የእግዚአብሔር ቃል መድሀኒቱ ነው-ተፈጥሯዊ መድሀኒት መፈወሻ መንገድ እንደሆነው ሁሉ ቃሉም እንደዚያው ነው፡፡ በሌላ አባባል መድሀኒት በራሱ ፈውስን የማምጣት ብቃት አለው፡፡በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ለሰውነታችሁ ፈውስ ፣ ብቃት ፣ ህይወት እና ችሎታ የማምጣት አለ፡፡

ታዲያ እንዴት ነው የምትወስደው? የእግዚአብሔር ቃል በልባችሁ ስር እየሰደደ ሲሄድ እና እዛው ሲቀር ብቻ ነው ለሰውነታችሁ ፈውስን የሚያፈራው፡፡ የጭንቅላት እውቀት ብቻ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ በሰውነታችሁ ፈውስ እንዲያመጣ የእግዚአብሔር ቃል አዕምሯችሁን እና ልባችሁን በማሰላሰል፣በማንበብ፣በመስማት፣በማገናዘብ እና በማብላላት ዘልቆ መግባት አለበት፡፡አንድ ጊዜ የእውነት ቃሉ ልባችሁን ዘልቆ ከገባ ለስጋችሁ ሁሉ ጤናን ያመጣል፡፡ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ልባችሁን ዘልቆ ይግባ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ዛሬ ፈዋሹን ቃልህን ማሰላሰልን መርጫለሁ፡፡ቃልህ በልቤ ውስጥ ጠልቆ ሲኖር ሳለ ፈውስህ ሰውነቴን እንደሚሞላው አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon