የእግዚአብሔር ትልቁ ፍላጎት (ደስታ)

የእግዚአብሔር ትልቁ ፍላጎት (ደስታ)

« …እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው»(ማቴ.1፡23)።

ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው ከኃጢአታችን መዋጀት እንድንችል፣ እግዚአብሔርን እንድናውቅና በህይወታችን የእርሱን ዋና ነገር መለማመድ እንድንችል ነው። እርሱ ከእና ጋር የጠበቀ ህብረት ሊያደርግ ይፈልጋልና በእኛ ሁሉም ነገር ል እንድንጋብዘው ይፈልጋል። ለዚህ ነው አንዱ የእግዚአብሔር ስም አማኑኤል የተባለው ትርጉምም «እግዚአብሔር ከእኛ ጋር» የሚል ነው። እርሱ ከእና ጋር መሆን ይፈልጋል፣ በቅርብነት በህይወታችን ውስጥ ሊሳተፍ ይፈልጋል። እርሱ ድምጹን እንድናውቅና እንድንከተለው ይፈልጋል።

የእግዚአብሔርን ፈቃድ በቀጥታ ከእርሱ በግልጽ እንሰማለን። እርሱ በግራቀ መጋባትና በፍርሃት እንድንኖር አያደርግም። እኛ ወሳኞች፣ ዋስትናና ያለንና ነጻነት ያለን ነን። እያንዳንዳችን ፍጻሜያችን እንድናሳካና ነእርሱ እቅድ ውስጥ በሙላት እንድንመላለስ ይፈልጋል። አዎን እኛ ከእግዚአብሔር በግላችንና በቀረበ ወዳጅነት ልንሰማ እንችላለን። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የጠለቀ ህብረት የሚመሠረተው ከእርሱ ጋር ካለን የቀረበ ግንኙነት ላይ ነው። እርሱ ለእኛ ስለሚናገር ስለዚህ እና በእርሱ የምንመራ፣ ሁሌ የምንታደስና የምንነቃቃና በመደበኛነት አዲስ ህወት የምንመራ እንሆናለን።

ለማንኛውም ሰው የመስማት የመጀመሪያው እርምጃ ከእግዚአብሔር ጨምሮ በትኩረት መስማት ነው። ጆሮህን ወደ እርሱ አዘንብልና ተረጋግተህ ስማው። እርሱ እንደሚወድህ ለአንተ ይናገራል። እግዚአብሔር ያንተን ፍላጎት (የሚያስፈልግህን) ሊያሟላ ይፈልጋልና አንተ ክምታስባውና ከምትገምተው በላይ እጅግ አብልጦ ያደርጋል (ኤፌ.3፡20 ተመልከት)። እርሱ ፈጽሞ አይተውህም ወይም አይጥልህም (ዕብ.13፡5 ተመልከት)። እርሱን ስማውና በየዕለቱ ህይወትህ እርሱን ተከተል።አንተ የእግዚአብሔር ነህ፤ አንተ አንዱ የእርሱ በግ ነህ፤ በጎች ደግሞ የእረኛቸውን ድምጽ ይሰማሉ፤ የእንግዳ (የሌላውን ድምጽ) ድምጽ ሲመጣ ግን ፈጽሞ አይከተሉትም (ዮሐ.10፡4 – 5 ተመልከት)። አንተ ከእግዚአብሔር መስማት ትችላለህ፤ ይህ እንደ ክርስቲያን አንዱ የርስትህ ክፍል ነው። ይህ ካልሆነ መቼም አታምንም።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ለአንተ የእግዚአብሔር ስጦታ አዲስ ህይወት ከጽድቅ፣ ከሰላም፣ከደስታና ከእርሱ ጋር ከመጣበቅ ጋር ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon