
ሕይወትን የሚወድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኮል ከመናገር ይከልክል፡፡ – 1 ኛ ጴጥ 3፡10
የምትናገሯቸውን ቃላት ሀይል ብትረዱ የህይወታችሁ አካሄድ ሊቀይር ይችላል! አፋችሁ ለእግዚብሔርም ሆነ ለሰይጣን ሀይለኛ መሳሪያ ነው፡፡በሌላ ቋንቋ ገንቢ፣ሰውን ከፍ የሚያደርግ፣ነገሮችን ወደ ህይወታችሁ እንዲመጡ የሚያበረታታ ወይም አፍራሽ፣ አሳዛኝ እንዲሁም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር መናገር ትችላላችሁ፡፡
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ሀይል እንዴት መጠቀም እንደምችል በህይወቴ ስላሉት ተራሮች ከማውራት ይልቅ ተራሮችን መናገር ተምሬያለሁ። የቃሉን እውነት ለሁኔታዎቼ መጠቀምን ተምሬያለሁ እናም በጊዜ ብዛት ገንቢ እና ዘላቂነት ያለው ውጤት አይቻለሁ፡፡
አፍ እንደ እስክርቢቶ ልባችሁ ደግሞ እንደ ደብተር ነው፡፡አንድን ነገር ደጋግማችሁ ስትሉት ውስጣችሁ ይገባና እናንተን ይሆናል፡፡ለማድረግ መታገል ያለባችሁ ነገር አይደለም ማንነታችሁ ነው፡፡
የሰይጣን አፍ ከመሆን ይልቅ የእግዚአብሔር አፍ መሆን ይሻለኛል፡፡የርሱን እውነት ተናግሬ ህይወቴን ማጣጣም ነው የምፈልገው፡፡
አንደኛ ጴጥሮስ 3፡10 ሕይወትን የሚወድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኮል ከመናገር ይከልክል ይላል፡፡መልካም ቀኖችን ልታዩ ትወዳላችሁ? የእግዚብሔርን ነገሮች በህይወታችሁ ላይ ለመናገር አንደበታችሁን ተጠቀሙበት!
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ አንደበቴ በአንተ ወይም በጠላት መጠቀሚያ ሊሆን የሚችል ሀይለኛ መሳሪያ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡አንደበቴን ለአንተ አስገዛለሁ፡፡እውነትህን በህይወቴ እና በሌሎች ሰዎች ህይወት ላይ እንዴት መናገር እንደምችል አሳየኝ፡፡