የእግዚአብሔር ፍቅር ሊለወጠን በቂ ነው

የእግዚአብሔር ፍቅር ሊለወጠን በቂ ነው

« … ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?» (ሚል.3፡2)።

እግዚአብሔር የየራሱ የሆነ የሚያነጥር እሳት በመጠቀም ይለውጠንና እርሱ እንድንሆን የሚፈልገውን ህዝብ እንድንሆን ያደርገናል። እኔ ያረጋገጥሁት ነገር ቢኖር መለወጥ ቀላል ነገር አይደለም። እኔ ከሰላሳ ዓመታት በላይ የእግዚአብሔርን ቃል ሳጠና ነበርና እኔ አሁንም ለተለያዩ ነገሮች የሚሰራ እንዲሆን በዚሁ ላይ ነኝና እግዚአብሔር በአንዳንድ መንገዶች እንዲለውጠን ለማድረግ እፈቅድለታለሁ። አሁንም ድረስ አንዳንድ እንድሆን የማልፈልጋቸው ሥፍራዎች አሉ፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁንና እንድሆን የምጠቀምባቸው ሥፍራዎች ላይ አይደለሁም።

እግዚአብሔር የሚጠራ እሳት በመላክ እንድንለወጥ በሚያስፈልገው የእኛ ባህርይን ሲገልጥልን እኛ ግትሮችና ንስሀ ለመግባት ፈቃደኞች ካልሆንን ከዚያ ፍቅር ግትርነትን ያገኘዋል። ይህንን ላብራራው፣ እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነ እናውቃለን፣ እንዲሁም እግዚአብሔር እርሱ ቀናተኛ አምላክ ነው። እርሱ በእኛ ውስጥ የእርሱ ያልሆነ በሌላ ሰው የተያዘ ምንም ሥፍራ እንዲኖር አይፈልግም። እናም እግዚአብሔር ራሱ፣ ፍቅር ሆነው እና የእርሱን መንገድ እስክናገኝ ድረስ እርሱ ቀናተኛ፣ ግትርና ከእና ጋር የተጠበቀ ይሆናል። ፍቅር (እግዚአብሔር) እኛ ባንፈልጋቸውም መሆን የሚያስፈልገንን እንድንሆን የሚረዱንን ነገሮች ያሳየናል (ይገልጥልናል)።

እሳት ማንኛውንም ርኩሰቶች የሚበላና የእግዚአብሔርን ክብር የሚያንጸባርቁትን ነገሮች በእኛ ውስጥ እንዲኖሩ ይተዋቸዋል። ለዓመታት በአሮጌዋ ጆይስ ሜየር ውስጥ ያሉ ብዙ ነገሮችን በእግዚአብሔር በሚያቃጥል እሳት ሲበሉ ነበር። በእርግጥ እነዚህ ነገሮች ቀላል አልነበሩም፣ ነገር ግን በእውነት እነዚህ ነገሮች አስፈላጊዎች (ተገቢዎች) ነበሩ።

የእግዚአብሔር የሚያጠራ እሳት በተለያዩ መንገዶች ወደ እኛ ሊመጡ ይችላሉ። ምናልባት አንድ ነገር እንዳናደርግ ሊያስቆመንና ሌላ አንድ ነገር እንድናደርግ ሊያስጀምረን በልባችን ውስጥ በሚያነቃን ጉሰማ ሊሠራ ይችላል። ወይም ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል በኩል በሚናገርበት ጊዜ የወቀሳ ስሜት ሊሰማህ ይችላል። ወይም ከመንፈስ ቅዱስ በመንፈስህ በቀጥታ የሚመጣ ድምጽልትሰማ ትችላለህ። ይሁንም እንጂ ይህ ሲሆን እግዚአብሔር ወደ ህይወትህ የሚያጠራ እሳቱን እየላከልህ ነው። ይህ በሚሆንበት ጊዜ እንዳትቃወመው ተጠንቀቅ ነገር ግን እግዚአብሔርን በመታመን እሳቱ ሥራውን እንዲሠራ ፍቀድለት።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ እግዚአብሔር በየዕለቱ እየለወጠህ ነውና፤ ስለዚህ ትላንትና ከነበርህበት ይልቅ ዛሬ አንተ የሆንከው የተሻለ የበለጠ ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon