የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ይመስላል?

የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ይመስላል?

በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣እንደበጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን… – ኤፌ 1፡5

ፍጹም ሳንሆን ለምንድነው እግዚአብሔር የሚወደን?ምክንያቱም ስለሚፈልግ-ያስደስተዋል፡፡ተግባሮቻችን ምንም እንኳን በሀጢያት የተሞሉ ቢሆኑም እኛን መውደድ ተፈጥሮ ነው፡፡

እግዚአብሔር ክፉን በመልካም ያሸንፋል(ሮሜ 12፡21ን ተመልከቱ)፡፡ይህንንም ያደረገው ሀጢያትን ስንሰራ ጸጋው ከሀጢያታችን እንዲበልጥ ያተገደበውን ጸጋውን በእኛ ላይ በማፍሰስ ነው፡፡ለእግዚአብሔር አለማፍቀር ከባድ እንደሆነው ሁሉ ለእኛም ደግሞ እርሱ እኛን መውደዱን እንዲያቆም የሚያደርግ ነገር ማድረግ የማይሆን ነገር ነው፡፡

እግዚአብሔር የሚወደን ተፈጥሮው ስለሆነ ነው፡፡እርሱ ፍቅር ነው(1ኛ ዮሐ.4፡8ን ይመልከቱ)፡፡ሁልጊዜ የምናደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ ላይወደው ይችላል፡፡ነገር ግን ይወደናል፡፡የእግዚአብሔር ፍቅር ሀጢያታችንን ይቅር የሚለው፣የስሜታችንን መቁሰል የሚፈውሰው እና የተሰበረውን ልባችንን የሚጠግነው  ሀይል ነው (መዝ.147፡3ን ይመልከቱ)፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ አይደለም፤በእርሱ ላይ እንጂ የተመሰረተው በእኛ ላይ አይደለም፡፡አንድ ጊዜ እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ካላችሁ ነገር ወይም ካልሰራችሁት ነገር ጋር እንደማይያያዝ መሆኑን አንዴ ከተረዳችት በኋላ የሚያስደንቅን ግኝት ትለማመዳላችሁ፡፡ፍቅሩን ለማግኘት መሞከራችሁን አቁማችሁ በቀላሉ ተቀብላችሁ በእርሱ መደሰት ትችላላችሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ አስደናቂ ነው፡፡በፍቅርህ ላይ ማተኮር በአንተ መልካምነት እንጂ በእኔ ድርጊቶች ላይ የተመሰረተ እንዳልሆነ ያሳስበኛል፡፡ለእኔ ያለህን ፍቅር መቀበል እንድችል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon